የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር፤ የSABC ደንብ ከሳንሱር የሚቆጠር ነዉ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 14 2008ማስታወቂያ
የደቡብ አፈሪቃ ማሰራጪያ ድርጅት (SABC) የተሰኘዉ የሐገሪቱ ትልቅ መገናኛ ዘዴ አዲስ ያወጣዉ ደንብ የድርጅቱን ሐላፊዎች ከጋዜጠኞች ጋር እያጋጨ ነዉ።የድርጅቱ ባለሥልጣናት ደንቡን አናከብርም ያሉ ስምንት ጋዜጠኞችን አባርረዋል ወይም ከሥራ አግደዋል።ጋዜጠኞቹ በበኩላቸዉ አዲሱ ደንብ በሐገሪቱ የተደረገገዉን ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ እና የመዘገብ ነፃነትን የሚፃረር ነዉ ባዮች ናቸዉ።የተለያዩ ማሕበራትና የመብት ተሟጋች ድርጅቶችም ለጋዜጠኞቹ ድጋፋቸዉን እየገለጡ ነዉ። የደቡብ አፍሪቃ ተባባሪ ዘጋቢያችንን አነጋግረነዋል።
መላኩ አያሌዉ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ