ደቡብ አፍሪቃ፤ አል በሽር ሃገሪቱን እንዳይለቁ
እሑድ፣ ሰኔ 7 2007ማስታወቂያ
አል በሽር ከአገር እንዳይወጡ ፍርድ ቤቱ ዉሳኔዉን መራዘሙን የደቡብ አፍሪቃ የብዙኃን መገናኛዎች በመዘገብ ላይ ናቸዉ። የደቡብ አፍሪቃ ገዥ ፓርቲ « ANC» በበኩሉ «ICC» ጥቅም የሌለዉ ተቋም ነዉ ሲል ዉሳኔዉን አስተባብሏል። ፕሬዚዳንት ኦመር አል በሽር በቁጥጥር ስር የመዋል ጥርጣሪ እያለባቸዉ ነዉ የአፍሪቃ ሕብረት ስብሰባ ላይ ለመገኘት ትናንት ወደ ደቡብ አፍሪቃ ያቀኑት።
አል በሽር በጦር ወንጀለኝነት እና በጅምላ ጭፍጨፋ ሰብዓዊ ፍጡር ላይ ከፍተኛ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት «ICC» በጎርጎረሳዉያኑ 2009 እና 2010 አል በሽር እንዲያዙ የማሰርያ ትዕዛዝ መቁረጡ ይታወቃል። በደቡብ አፍሪቃ ፕሪቶርያ ፍርድ ቤት የሚገኙ አንድ ዳኛ ባሳለፉት ዉሳኔ ለረጅም ጊዜ የተወሰነዉ የማሰርያ ማዘዣ አዲስ ዉሳኔ እስኪያገኝ ኧል በሽር ደቡብ አፍሪቃን ለቀዉ መጓዝ አይችሉም። ደቡብ አፍሪቃ የዓለም አቀፉ የጦር ወንደለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት አባል በመሆንዋ፤ የተላለፈዉን የማሰርያ ትዕዛዝ ተፈፃሚ የማድረግ ግዴታ አለባት። በልማት ላይ የሚመክረዉና ዛሬ ጆሃንስበርግ ላይ የጀመረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ የሱዳኑ ፕሬዚዳንት በICC መያዝ አለመያዝ ወሬ ተጋርዶአል።
አዜብ ታደሰ
ልደት አበበ