1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዮናታን ተስፋዬ ጥፋተኛ ተባለ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 8 2009

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ምድብ ችሎት የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬን ጥፋተኛ ናቸው አለ። የሕግ ምሑሩ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፤ የፍልሥፍና መምሕሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ለአቶ ዮናታን በመከላከያ ምሥክርነት ተቆጥረው ችሎት ከቀረቡት መካከል ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/2d4P1
Yonatan Tesfaye Äthiopien
ምስል DW/Y.Geberegziabehr

(Beri. A.A)Yonatan Tesfaye guilty of terrorism for Facebook posts - MP3-Stereo

ወጣቱ ፖለቲከኛ የታሰሩት ቀስቃሽ ፅሁፎችን በፌስ-ቡክ «አስተላልፈዋል» በሚል  ክስ ነው። አቶ ዮናታን ጥፋተኛ የተባሉት የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀፅ 6ን በመተላለፍ መሆኑ ተሰምቷል። አንድ አመት ከአምስት ወር በላይ በእስር የቆዩት አቶ ዮናታን የቀረበባቸውን ክስ ለመከላከል እስር ላይ የሚገኙትን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ  ሊቀ-መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲናን እና አቶ በቀለ ገርባን፤ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ  ጨምሮ 10 ምሥክሮች አቅርበው የቀረበባቸውን ክሥ ሲከላከሉ ቆይተዋል። የሕግ ምሑሩ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም፤ የፍልሥፍና መምሕሩ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ለአቶ ዮናታንን በመከላከያ ምሥክርነት ተቆጥረው ችሎት ከቀረቡት መካከል ይገኙበታል። በወጣቱ ፖለቲከኛ ላይ የተያዘባቸዉ የወንጀል አንቀፅ ከእስር እስከ 20 ዓመት እስራት የሚያስፈርድ ነዉ።ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለመጪው ግንቦት 17 ቀጠሮ ይዟል። 


ዮሐንስ ገብረግዜአብሔር 


እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ