በአስራ አንድ አመቷ የተዳረችው ማሚት ሐብቱ
ሐሙስ፣ ጥር 4 2009ማስታወቂያ
ድህነት፣የትምህርት እና ኤኮኖሚያዊ አማራጮች እጦት ወላጆች ልጆቻቸውን በግዴታ ለመዳር ከሚያስገድዷቸው ጉዳዮች መካከል ቀዳሚዎቹ መሆናቸውን የግብረ-ሰናይ ድርጅቱ መረጃ ያትታል። በኢትዮጵያ ወንዶችም ሆነ ሴቶች ትዳር ለመመሥረት 18 ዓመት ሊሞላቸው እንደሚገባ ሕግ ቢደነግግም፣ በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እኩል ተግባራዊ አይደረግም። 15 ዓመት ሳይሞላቸው የሚዳሩ ሴት ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እድላቸው አነስተኛ ከመሆኑም ባሻገር የሰብዓዊ ጥሰትም ይገጥማቸዋል። ወደ መቀሌ የተጓዘው የዶይቼ ቬለ ወኪል ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር በ11 አመቷ በግዴታ የተዳረችውን ማሚት ሐብቱን አግኝቶ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ