1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩኤስ አሜሪካ እና ሶማልያ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 2 2001

ዩኤስ አሜሪካ የሶማልያ የሽግግር መንግስት በአክራሪ ሙስሊሞች አንጻር የጀመረውን ትግሉን እንደምትደግፍ አረጋገጠች።

https://p.dw.com/p/J5nY
ሼኽ ሻሪፍ ሼክ አህመድ
ሼኽ ሻሪፍ ሼክ አህመድምስል AP

ይህንን ያስታወቁት የዩኤስ አሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂለሪ ክሊንተን ከሁለት ቀናት በፊት በናይሮቢ ኬንያ ከሶማልያ የሽግግር መንግስት ፕሬዚደንት ሼኽ ሻሪፍ ሼክ አህመድ ጋር በተገናኙበት ጊዜ ነበር።

በሶማሊያ የአፍጋኒስታን፣ የፓኪስታን፣ የቼቺኒያ ዜጎችና ከስደት የተመለሱ ሶማሊያውያን በአክራሪው የአልሸባብ ቡድን ጥላ ስር ሆነው የሶማሊያ የሽግግግር መንግስትን እየተዋጉ እንደሆነ ተገልጿል። ሁኔታው ያሳሰባት ዩኤስ አሜሪካ አሽባሪዎችን ለመዋጋት በሚል ለሶማሊያ አርባ ቶን የጦር መሳሪያ መላኳ ይታወቃል። ሰሞኑን ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ሂላሪ ክሊንተን ከኬንያ ሆነው እንዳስታወቁት፤ የሶማሊያ የሽግግር መንግስትን የመደገፉ ሁኔታ እንደሚቀጥል ታውቋል። በአንፃሩ ለኤርትራ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክትም ተላልፏል።

አርያም ተክሌ/ማንተጋፍቶት ስለሺ