1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩኤስ አሜሪካ በሶማልያ የአየር ድብደባ አካሄደች

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 27 2006

የዩኤስ አሜሪካ ወታደራዊ አየር ኃይል በሰው አልባ አይሮፕላን በሶማልያ የሚገኙ የአሸባብ ሚሊሽያዎች ላይ የአየር ድብደባ አካሄደ። የአየር ጥቃቱ የተካሄደዉ ትናንት ሌሊት እንደሆን ተመልክቶአል።

https://p.dw.com/p/1D5S8
somalia milizen al-shabaab, al-shabab mogadischu
ምስል AP

በደቡብ ሶማልያ የታህታይ ሸበሌ ሀገረ ገዥ አብዱካዲር ሞሃመድ ኑር እንደተናገሩት፤ ጥቃቱ በተለይ ያነጣጠረዉ የአሸባብ መሪ በሆኑት አህመድ አብዲ ጎዳኔ እና በሌሎች የቡድኑ መሪዎች ላይ ነበር። የቡድኑ መሪዎች በጥቃቱ መገደል አለመገደላቸዉ በግልፅ የታወቀ ነገር ባይኖርም፤ በአየር ጥቃቱ የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ታውቋል። በሌላ በኩል በሶማልያ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ የከፍተኛ የረሃብ አደጋ ተደቅኖበታል፤ 220 ሽ ከአምስት ዓ,መት በታች የሆኑ ህፃናት በምግብ እጥረት እየተሰቃዩ ነዉ ሲል የመንግሥታቱ ድርጅት ስጋቱን ገልፆአል። ዩኤስ አሜሪካ በሶማልያ በሰው አልባ አይሮፕላን ስላካሄደችውን የአየር ጥቃት ከዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገናል።

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ