የHIV ምርመራ ሳምንት በድሬዳዋ
ማክሰኞ፣ የካቲት 24 2001ማስታወቂያ
በዚሁ ሳምንትም በርካታ ነዋሪዎች በደማቸው ውስጥ HIV መኖር አለመኖሩን ለማወቅ አገልግሎቱን ለመስጠት ወደ ተዘጋጁት ቦታዎች በመምጣት በፈቃደኝነት ይመረመራሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመስተዳድሩ በተለይ በገጠሩ አካባቢ በሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች ህብረተሰቡ በሽታውን ለመከላከል ይረዳል ብሎ ባመነው መሰረት ጋብቻዎች ከመፈፀማቸው በፊት የHIV ምርመራ መካሄዱ እንደ አንድ ቅድመ ግዴታ ተደንግጓል ። በሌላም በኩል በኢትዮጵያ ጅቡቲና ሶማሌላንድ መካከል የድንበር ተሻጋሪ የ HIV ክትትል ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ከድሬዳዋ ዘግቧል ።