1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የHIV መድሃኒት ክትትል

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 28 2005

UNAIDS በመድሃኒት ስርጭትና ቁጥጥር ረገድ ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገሮች ጋ ስትነፃፀር በተሻለ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የገለጸዉ በያዝነዉ ዓመት ግንቦት ወር ነዉ። እንደድርጅቱ ዘገባም በቫይረሱ አዲስ ከሚያዙት ይልቅ መድሃኒት የሚወስዱ ወገኖች ቁጥርም ከፍ ማለቱን ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/19bZy
ምስል AP

በሌላ ወገን በሀገሪቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በአንዳንድ አካባቢዎች ጸረ ኤች አይቪ መድሃኒት የሚወስዱ ወገኖች ቁጥር ቀንሶ መታየቱን የሚያመላክቱ መረጃዎች ይፋ ሆነዋል። ይህን የሚገልጹት ወገኖች ለዚህ እንደምክንያት የሚያነሱት መድሃኒት የሚወስዱ ወገኖችን አስመልክቶ የሚሠሩ የክትትል ሥራዎች መላላትን ነዉ።

የበሽታ መቋቋም አቅምን በማጠናከር የኤድስ ተህዋሲን የሚያዳክም መድሃኒት የሚወስዱ ወገኖች ቁጥር እየቀነሰ ስለምጣቱ የሚጠቁም ዝግጅት ከሳምንታት በፊት ማቅረባችን ይታወስ ይሆናል ብለን እንገምታለን። ይህ አስመልክቶ ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ አካላት አንዱ የሆነዉ HIV ቫይረስ በደማቸዉ የሚገኝ ወገኖች ያቋቋሟቸዉ ማኅበራት ጥምረት መድሃኒቱን ሰዎች አቋረጡ ሲባል የተለያዩ ምክንያቶችም አብረዉ ሊታዩ እንደሚገባ ለዶቼ ቬለ ለማብራራት ሞክሯል።

Esther Babalola HIV/AIDS in Sagamu, Nigeria, Medikamente
ምስል AP

አቶ ደረጀ አለማየሁ HIV ቫይረስ በደማቸዉ የሚገኝ ወገኖች ማኅበራት ጥምረት ሥራ አስኪያጅ መድሃኒት የሚወስዱ HIV ቫይረስ በደማቸዉ የሚገኝ ወገኞች እያቋረጡ ነዉ በሚል የቀረቡ ዘገባዎች መብራራት እንደሚኖርባቸዉ ያሳስባሉ። እንደ አቶ ደረጀ ገለጻ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስምንት መቶ ሰማንያ ገደማ የሚሆኑ የጤና ተቋማት መድሃኒት ለተጠቃሚዎች እየሰጡ ይገኛሉ። ሀገር አቀፍ ጥምረቱ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ወደሶስት መቶ ሰባ ስምንት የጤና ተቋማት ላይ በክትትሉ ረገድ አብሮ እየሠራ እንደሚገኝም ያመለክታሉ።

ከሳምንታት በፊት ጉዳዩን በማንሳት ተከታትለን እንደምንዘግብ ቃል መግታችን ይታወሳል፤ ዛሬም የመድሃኒት ክትትሉን በሚመለከት ምን እየተሠራ ነዉ? እሳቸዉ በኃላፊነት የሚገኙበት የማኅበራት ጥምረትስ በዚህ ረገድ ሚናዉ ምን ይሆን? ለአፍታ እንቃኛለን።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ