1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የEBC ኃላፊዎች ሹመት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 7 2009

እስከ ትናንት ድረስ የአማራ መስተዳድር የመገናኛ ብዙሐን ሐላፊ  የነበሩት አቶ ሥዩም መኮንን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነዉ ሲሾሙ፤ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነዋል

https://p.dw.com/p/2UPbO
Äthiopien Parlament Hailemariam Desalegn
ምስል DW/Y. G. Egziabher

(Beri.AA) Äth.Parliament-EBC - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሐገሪቱ መንግሥት የሚቆጣጠረዉን የኢትዮጵያ ማሰራጪያ ድርጅት (EBC በእንግሊዝኛ ምሕፃረ ቃሉ) ዋና ሥራ አስኪያጅና የቦርድ አባላት ሹመት አፀደቀ።እስከ ትናንት ድረስ የአማራ መስተዳድር የመገናኛ ብዙሐን ሐላፊ  የነበሩት አቶ ሥዩም መኮንን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነዉ ሲሾሙ፤ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ሹመቱን አስታክኮ አስተያየቶችን አሰባስቧል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ