1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«CPJ» ዓመታዊ ዘገባ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 4 2009

ድርጅቱ ትናንት ባወጣዉ ዓመታዊ ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ከዓለም አንደኛ ቱርክ፤ ሁለተኛ ቻይና ሆነዋል።ከሁለቱ ሐገራት ጋር ሲወዳደር ብዙ ጋዜጠኞችና መገናኛ ዘዴዎች የሌሉባቸዉ የምስራቅ አፍሪቃ ሐገራት ከ3 እስከ አምስት ያለዉን ሥፍራ ይዘዋል

https://p.dw.com/p/2UCqW
Logo CPJ
ምስል APTN

(Beri.WDC) CPJ Bericht 2016 - MP3-Stereo

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር፤በመክሰስ እና ማንገላታት፤ የመናገርና የመፃፍ ነፃነትን በማፈን በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ሰወስት የአፍሪቃ ሐገራት አንዷ መሆኗን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ አስታወቀ።ድርጅቱ ትናንት ባወጣዉ ዓመታዊ ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ በርካታ ጋዜጠኞችን በማሰር ከዓለም አንደኛ ቱርክ፤ ሁለተኛ ቻይና ሆነዋል።ከሁለቱ ሐገራት ጋር ሲወዳደር ብዙ ጋዜጠኞችና መገናኛ ዘዴዎች የሌሉባቸዉ የምስራቅ አፍሪቃ ሐገራት ከ3 እስከ አምስት ያለዉን ሥፍራ ይዘዋል።ግብፅ፤ኤርትራ እና ኢትዮጵያ።የዋሽግተን ዲሲዉ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ