1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ29 ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የመግባቢያ ሰነድ

ዓርብ፣ ጥር 17 2005

ከዚያን ወዲህ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ እስከማዘጋጀት የደረሱት ፓርቲዎች አሁን በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ አብረው ሲሰሩ ወደፊት ደግሞ ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር እቅድ እንዳላቸውም አቶ አሥራት ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/17Rnb
An Ethiopian woman casts her vote at a polling station in Addis Ababa, Ethiopia Sunday, May 15, 2005 during the third democratic elections in Ethiopia's 3,000-year history. (AP Photo/Karel Prinsloo)
ምስል AP

ከሚያዚያው የአካባቢና የአዲስ አበባ አስተዳደር ምርጫ ራሳቸውን ያገለሉት 29 የፖለቲካ ፓርቲዎች አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ሰነድ አዘጋጁ ። ከፓርቲዎቹ የተውጣጣው ጊዜያዊ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ረቂቅ ሰነዱ ለፓርቲዎቹ የተበተነ ሲሆን ፓርቲዎቹም ነገ በሚያካሂዱት ስብሰባ በረቂቅ የመግባብያ ሰነዱ ላይ ይመክራሉ ። የሰነዱን ምንነትና አላማ

የ29 ኙ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አሥራት ጣሴ ለዶቼቬለ ተናግረዋል

መጀመሪያ 33 አሁን ደግሞ ቁጥራቸው ወደ 29 ዝቅ ያለው እነዚሁ ፓርቲዎች የተሰባሰቡት በአዳማ ከተማ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው የምርጫ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት በተገኙበት አጋጣሚ ነበር ።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Wählerin in Oromia, Äthiopien 23.Mai 2010 Thema: bei Äthiopiens Parlamentswahl 2010 gibt diese Frau am frühen Nachmittag in der Provinzhauptstadt der Oromia-Region, Nazareth, ihre Stimme ab. Der Wahltag verlief friedlich Schlagwörter:Wahl Äthiopien 2010, Stimmabgabe, Polls, Voting Ethiopia 2010
ምስል DW

በወቅቱም በጋራ 18 ጥያቄዎችን ለምርጫ ቢቦርድ ቢያስገቡም ጥያቄዎቻቸው ውድቅ ስለሆኑባቸው ራሳቸውን ከሚያዚያው ምርጫ ለማግለል መገደደቻውን አስታውቀዋል ። ከዚያን ወዲህ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ እስከማዘጋጀት የደረሱት ፓርቲዎች አሁን በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ አብረው ሲሰሩ ወደፊት ደግሞ ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ የማሸጋገር እቅድ እንዳላቸውም አቶ አሥራት ተናግረዋል ።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Büro des "National Electoral Board of Ethiopia" (NEBE) Thema: Die Nationale Wahlkommission Äthiopiens, NEBE, wacht über den Wahl- und Auszählungsprozess Schlagwörter: "National Electoral Board of Ethiopia" (NEBE), Äthiopien 2010, Wahl Äthiopien 2010
ምስል DW

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀው በሁለት ተከታታይ ምርጫዎች ያልተሳተፈ ፓርቲ እውቅና ይነፈጋል ። አቶ አሥራት ከ29 ኙ ፓርቲዎች በዚህ አሠራር ችግር ላይ የሚወድቅ አለመኖሩን ገልፀዋል ። ሆኖም ይህ ያሰጋል ተብሎ ባላመንበት አካሄድ መሳተፍ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል ።

በምርጫ አብሮ መሥራት ተገቢ መሆኑን ያሳወቁት አቶ አሥራት ሌላውን እየተዉ መሄድ ግን ወደ ፖለቲካ ፍጥጫ የሚያመራና የሚደገፍ አሥራርም እንዳልሆነ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል ።  

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ