1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ29ኙ ፓርቲዎች አስተባባሪ ኮሚቴ መግለጫ

ቅዳሜ፣ ጥር 25 2005

ያቀረቧቸዉ ጉዳዮች ትኩረት ካላገኙ በቅርቡ በሚካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ እንደማይሳተፉ ያመለከቱት ፓርቲዎች የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲዎችን አስመልክቶ ከመንግስት ባለስልጣን የተሰጠ አስተያየት ቅር እንዳሰኛቸዉ በመግለጫቸዉ አመለከቱ።

https://p.dw.com/p/17Wok
ምስል Solomon Mengist

የኢህአዴግ ምክር ቤት ፀሐፊ እና የድርጅቱ የምርጫ ኮሚቴ አስተባባሪ አቶሬድዋን ሁሴን ሰሞኑን ተቃዋሚዎችን አስመልክተዉ ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን የሰጡት መግለጫ እንዳሳዘናቸዉ የ29ኙ የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች አስተባባሪ ኮሚቴ ገለፀ። ኮሚቴዉ ቅሬታዉን በፅሁፍ መግለጫ ይፋ ያደረገ ሲሆን የአስተባባሪዉ ኮሚቴ ሊቀመንበርም ለዶቼ ቨለም ጉዳዩን አብራርተዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ