የ29ኙ ተከሳሽ ሙስሊሞች የዛሬዉ ችሎት
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 2005ማስታወቂያ
ተከሳሾች የአምነት ክህደት ቃላቸውን በሰጡበት በዚህ የፍርድ ቤት ሂደት፤ ህገመንግሥቱን ተከትለው ከመንቀሳቀስ በስተቀር አንዳች የወንጀል ተግባር አለመፈጸማቸውን እንደገለጹ ፣ ከዜና አውታሮች የተገኘው ዜና ያስረዳል። አንዳንድ የክስ ሐረጎች በተካሳሾች ክርክር ተሻሽለው መቅረባቸው ተወስቷል። ጉዳያቸው እንደገና በሚመጣው ወር ይታያል ። በሥፍራው ተገኝቶ የነበረውን የአዲስ አበባውን ዘጋቢአችንን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔርን ተክሌ የኋላ በስልክ አነጋግሮት ነበር።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ