የዓለም ተግዳሮቶች እና ተስፋዎች
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 24 2009ማስታወቂያ
ጎርጎሮሳዊው 2017 ዓም ከገባ ዛሬ ሁለተኛ ቀን ተቆጠረ ። ዘመኑን በጎርጎሮሳዊው ቀመር የሚያሰላው ዓለም ዓለም ባለፈው ዓመት የደረሱ ውድመቶች ሰቆቃዎች እና ስደት እንዳይደገም በመመኘት አዲሱን ዓመት ተቀብሏል ።ይሁንና በ2017፣ ከሁለት ቀናት በፊት ከተሸኘው ከ2016 ችግሮች ምን ያህሉ ይቀረፋ ሉ ስንቱስ ይወረሳሉ ? አዲሱ ዓመትስ የሰላም ፣የመግባባት እና የብልጽግና ዓመት ወይንስ የአምባጓሮ የብጥብጥ እና የፍጥጫ ዓመት ይሆናል ? በዚህ ወቅት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸው ። የዛሬው ማህደረ ዜና በ2017 የዓለም ተግዳሮቶች እና ተስፋዎቿ ላይ ያተኩራል ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ አዘጋጅቶታል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ