1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2008 አበይት ክንዉኖች

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 21 2001

«አዎ እንችላለን» የአመቱ ምርጥ ጥቅስ

https://p.dw.com/p/GPHV
አዎ-ቻሉምስል AP Graphics/DW

ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።ኦባማ የማችለዉን-ችለዉበት፣የማይደፈሩት ቡሽ በጫማ ተደፍረዉበት፣ ቢሊየኖሮች በአጭበርባሪነት ተዋርደዉባት፤አለም ከስሮ-የማይሆነዉ ሆኖበት፣-በአክራሪ ሙስሊምነት የሚወቀሱት፣ በአሸባሪዎች አዝማችነት የሚወነጀሉት አሕመዲኒጃድ የክርስቶስ ልደትን ዘክረዉ-ያልጠበቀባቸዉን-ብለዉበት ሁለት ሺሕ ስምት ሩጫዉን አገባደደ።በአመቱ ሒደት ከአዉሮጳና አፍሪቃ ዉጪ ያለዉን አለም አበይት ክንዉኖች ባጭሩ እንቃኛለን።አብራችሁኝ ቆዩ።
ባራክ ሁሴይን ኦባማ።ጥር ሰወስት ለትልቁ መሪነት አይደለም ለመለስተኛ ተቋም ሐላፊነት፣ ከችሎታ እዉቀት ይልቅ የቆዳ-ንጣት፣ የዘር-ሐረግ ፅዳት፣ የሐብት ክምችት፣ የልምድ ብዛት በሚያስመርጥበት አለም ከጥቁር፣ ያዉም ከደሐይቱ ኬንያ ደሐ መጤ ተማሪ የሚወለዱት፣ በፖለቲካዉ ሽጠራ ያልተካኑት ሴናተር በትልቂቱ ሐገር ትልቅ ግዛት ትልቅ ተቀናቃኛቸዉን ማሸነፋቸዉ ጉድ አሰኘ---

George W Bush Schuhattacke
ጫማዉ ሳታቸዉ ታሪኩ አብሮቸዉ ይኖራልምስል AP