1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2005 ዋና ዋና ፖለቲካዊ ክንዉኖች

ሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2005

የመለስ ዜናዊ አስተሳሰብና ምግባር ሕዝብን በተለይም ፖለቲከኞችን በተራራቀ ተቃራኒ ጫፍ እንዳቆሙ መሞታቸዉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበጎ ወይም በመጥፎ፥ ወይም በሁለቱም መሐል-ክፉኛ መንካቱ እንደማይቀር ያኔ ተብሎ ነበር።አሁንም አልቀረም።

https://p.dw.com/p/19eQm
Ethiopian Prime Minster Hailemariam Desalegn (L) speaks during a meeting with his Somali counterpart Hassan Sheikh Mohamud (R- nicht im Bild - Anm. Bildredaktion) in Addis Ababa on November 28, 2012. Hailemariam reiterated Ethiopia?s commitment to keeping its troops in Somalia until African Union forces take over Ethiopian strongholds, but did not provide a timeline. Ethiopia sent troops and tanks into Somalia in November 2011 to support AU and Somali troops fighting Shebab extremists. They have since captured key towns from the Islamist militants, including Baidoa and Beledweyne. AFP PHOTO/JENNY VAUGHAN. (Photo credit should read JENNY VAUGHAN/AFP/Getty Images)
ምስል Getty Images

የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚንስትር ተሸኙ።

ሁለት ሺሕ አራትም ተሰናበተ።እና አዲስ ዓመት።ሁለት ሺሕ አምስት።ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃና ጳጳሳት እና፥በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞት ማግስት የባተዉ ሁለት ሺሕ አምስት ካዲስ መሪ፥ ካዲስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሹመት ጋር አዲስ ተስፋ አጭሮም ነበር።ዓመቱ ዛሬ-አርጅቶ ሊሰናበት ሁለት ቀን ቀረዉ።የዓመቱን የኢትዮጵያ አበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች እየጠቃቀስን፥ተስፋዉ መጠዉለግ-መፅደቁን፥ ላፍታ እንቃኛለን።አብራችሁኝ ቆዩ።

ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ጳዉሎስ፥ እና ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ባንድ ተከታትለዉ መሞታቸዉ ለየአፍቃሪ ደጋፉዊቻቸዉ ታላቅ መርዶ፥ ለብዙ ኢትዮጵያዊ አሳዛኝ፥ ለሌላዉ አሳሳቢ፥ ለሐይማኖትና ለፖለቲካ አስተንታኖች አነጋጋሪ ነበር።

ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በጠላቶቻቸዉ ዓይን ጨካኝ፥ አረመኔ፥ በተቃዋሚዎቻቸዉ አመለካከት አምባገነን፥ ሥልጣን ወዳድ ናቸዉ።ለቤተ-ሠቦቻቸዉ ግን ባለቤታቸዉ ወይዘሮ አዜብ መስፍን እንዳሉት ጠላት ተቃዋሚዎቻቸዉ ከሚሏቸዉ ተቃራኒ ናቸዉ።ነበሩ። አፍቃሪ፥ መካሪ፥ አዛኝ፥ ሩሕሩሕ፥ ነበሩ።

ነሐሴ-ሃያ ሰባት ሁለት ሺሕ አራት።ለወዳጆቻቸዉ ብልሕ ፖለቲከኛ፥ የአፍሪቃ ባለዉለታ፥ ለተከታዮቻቸዉ እና ለሥልጣን ወራሾቻቸዉ ደግሞ፥ ካንጀትም ሆነ ካንገት፥ ከመሪዎችም ታላቅ መሪ፥ አርቆ አሳቢ፥ ለሐገር ለወገን ተቆርቋሪም ነበሩ።እንዲያዉም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንደሚሉት መለስ ልዩ ሰዉ ነበሩ።


የመለስ ዜናዊ አስተሳሰብና ምግባር ሕዝብን በተለይም ፖለቲከኞችን በተራራቀ ተቃራኒ ጫፍ እንዳቆሙ መሞታቸዉ የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበጎ ወይም በመጥፎ፥ ወይም በሁለቱም መሐል-ክፉኛ መንካቱ እንደማይቀር ያኔ ተብሎ ነበር።አሁንም አልቀረም።

መለስ በተቀበሩ በሳምቱ ሁለት ሺሕ አምስት እንደ አዲስ ዓመት ሲብት ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞችን ጨምሮ በሺሕ የሚቆጠሩ እስረኞች በምሕረት መፈታታቸዉን የኢትዮጵያ መንግሥት ማወጁ፥ የአዲሱ ዓመት አዳዲስ መሪዎች አሮጌዉን ከፋፋይ መርሕ ከአሮጌዉ ዓመት ጋር ለማሰናበት ፍንጭ ማሳየታቸዉ መስሎ ነበር።

ከእስረኞቹ የመፈታት ዜና በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ጋር ለመደራደር መወሰኑን አስታዉቆም ነበር።ኦብነግ የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መንግሥት ለረጅም ጊዜ ባሽባሪነት የወነጀለዉ፥ ከሁለት ሺሕ ሁለት ጀምሮ ደግሞ ከአል-ኢዳ፥ ከአሸባብ፥እና ከሁለት ሐገር በቀል ድርጅቶች ጋር በሕግ-በአሸባሪነት የፈረጀዉ ቡድን ነዉ።

በዚሕም ሰበብ በመለስ ሞት ማግሥት አዳዲሶቹ መሪዎች ከኦብነግ ጋር ለመደራደር መስማማታቸዉን ሲያስታዉቁ፥ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ ተስፋ ማጫሩ አልቀረም።በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ናይሮቢ ኬንያ ዉስጥ በኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስትር ሲራጅ ፈርጌሳና በኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ በአብዱረሕማን መሕዲ መካካል የተደረገዉ ድርድር እንዲደረግ የወሰኑት የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከመሞታቸዉ በፊት መሆኑ ሲነገር ግን ተስፋዉ የአዲሱ ዓመት ፀጋ፥ የአዲሶቹ መሪዎችም ብልሕነት እንዳልሆነ ግልፅ ሆነ።እስረኞቹ የተለቀቁትም በመለስ ዉሳኔ እንደነበር ተነግሯል።

የሁለቱ ወገኖች ተደራዳሪዎች በድርድሩ ሥነ-ሥርዓታዊ ጉዳዮች ተስማምተዉ፥ ለመስክረም ማብቂያ ለሁለተኛ ዙር ድርድር ለመገናኘት ተቀጣጥረዉ ነበር።መንግሥት አማፂዉ ቡድን ሕገ-መንግሥቱን ካልተቀበለ አልደራደርም በማለቱ፥ አማፂዉ ቡድን ቅድመ ሁኔታዉን ባለመቀበሉ ቀጠሮዉ-በቀጠሮ ቀረ።ተስፋዉም ቢያንስ ለዚሕ ዓመት ተጨናጎለ።

ተስፋ የማይቆርጠዉ ወይም ተስፋ ላለመቁረጥ፥ ተስፋ የሚያደርገዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ ተስፋ የሚያደርግበት ሰበብ ምክንያት አላጣም።የአዲሱ መሪዉ ቃል ዋናዉ ነበር።የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞት ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ሥልጣን በጊዚያዊነት የያዙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚንስትርነትቱን ሥልጣን በይፋ ተረከቡ።

መስከረም አስር።አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ኋላ እንዳሉት የዚያን ቀን ያደረጉትን ንግግር ፍሬ ሐሰብ ከማርቀቅ በስተቀር ንግግሩን የፃፉት ሌሎች ናቸዉ።ንግግሩን እንደ ኦጋዴኑ ድርድር ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የወሰኑት ወይም ፅፈዉ የተዉት ነዉ ማለት ግን አይቻልም።የንግግሩ ይዘት፥ ቃሉም ብዙ አዲስ አይደለም።ግን የአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ነዉ።የሐይለ ማርያም ደሳለኝ።

ሁሉም ተባለ።የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ጥሪ፥ የነፃ ጋዜጠኞች አቤቱታ፥ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስሞታ፥ የሙስሊሞች ጩኸትም ቀጠለ።ታሕሳስ መባቻ። የአል-ጀዚራዋ ጋዜጠኛ አዲሱን የጠቅላይ ሚንስትር ጠየቀች።

«ሙስሊሞችን በተመለከተ በቀጠለዉ የተቃዉሞ ሠልፍ ምክንያት (እና በሌላም ምክንያት) በሐገሪቱ ዉስጥ ብዙ ችግሮች አሉባችሁ።በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ታስረዋል።ብዙዎቹ እንደሚሉት መንግሥት ሐባሽ የተሰኘዉን የእስልምና (ሐራጥቃ) በሕዝቡ ላይ በሐይል ጭናችኋል፥ መንግሥት ሐይማኖቱን በሐይል ባዲስ መልክ ለመቅረፅ ጠንካራ እርምጃ ወስዷል ይላሉ።ጠንካራ እርምጃ ነዉ።»

ጠቅላይ ሚንስትሩ መለሱ።

«እንደሚመስለኝ ይሕ የአናሳዎች ድምፅ ነዉ።የአብዛኞቹ ድምፅ አይደለም።የአብዛኞቹ ሙስሊሞች ጥያቄ የራሳቸዉ የአስተዳደር ሥርዓት እንዲኖራቸዉ ነዉ።መንግሥት በነሱ የአስተዳደር ሥርዓት ዉስጥ የሚያገባዉ የለም።ለሐይማኖት ያልወገነ መንግሥት ነዉ ያለዉ።ሕገ-መንግሥቱም መንግሥት በሐይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ ይደነግጋል።»

ጥር ማብቂያ።ጠቅላይ ሚን’ስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ «በሐይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ያሉት መንግሥት የሚቆጣጠረዉ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጉዳያቸዉ በፍርድ ቤት የሚታይ የሙስሊም መሪዎችን በአሸባሪነት የሚወነጅለዉን ፊልም አሰራጨ።ርዕስ፥ ጅሐዳዊ ሐረካት።

ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ለአል-ጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ በፖለቲካ ምክንያት የታሠረ አንድም ሰዉ እንደሌለ ተናግረዉ ነበር። ጥር ማብቂያ። ዓለም አቀፉ የሠብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሑዩማን ራይትስ ዋች ባወጣዉ ዘገባዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከጥር ሁለት ሺሕ አራት እስከ ታሕሳስ ሁለት ሺሕ አምስት በነበረዉ አንድ ዓመት ብቻ ሰላሳ የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች በአወዛጋቢዉ የፀረ-ሽብር ሕግ ተወንጅለዉ እስራት ተበይኖባቸዋል።

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ከሞቱበት እስከ ዓመቱ አጋማሽ ድረስ የዉጪ እና የሐገር ዉስጥ በሚል ለሁለት የተከፈሉት የሐይማኖት አባቶች ይታረቃሉ የሚል ተስፋ አሳድሮ ነበር።ድርድር፥ ዉይይትም ነበር።የካቲት-ሁሉም ቀረ።የሐገር ዉስጡ ሲኖዶስ የዉጪዉን ጥያቄ ዉድቅ አድርጎ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ሾመ።

ሚያዚያ፥ ምርጫና ጉብኝት ነዉ።መስከረም ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል ገብተዉ ነበር።

ሚዚያ ላይ ሠላሳ ሠወስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድን ጨምሮ ከመንግሥትና ከገዢዉ ፓርቲ ይደርስብናል ያሉት ጫና እንዲቃለልላቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ሆነብን በሚል ከአካባቢያዊና ከከተሞች አስተዳድር ምርጫ እራሳቸዉን አገለሉ።ገዢዉ ፓርቲ እና ተባባሪዎቹ ብቻቸዉን ተወዳድረዉ አሸነፉ።

ጠይላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ከአዉሮጳ ሕብረትና ከፈረንሳይ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር ብራስልስን፥ ሽትራስቡርግንና ፓሪስን የጎበኙትም ሚዚያ አጋማሽ ነበር።

ግንቦት፥ የአሕሪቃ መሪዎች የአፍሪቃ ሕብረት የተመሠረተበትን ሐምሳኛ ዓመት አዲስ አበባ ዉስጥ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አከበሩ።መሪዎቹ በተሰናበቱ በሳምንቱ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉ የተቃዉሞ ሠልፍ አዲስ አበባ ዉስጥ ተደረገ።ከ1997 ወዲሕ ሕዝብ፥ መንግሥትን በመቃወም አደባባይ ሲወጣ የመጀመሪያዉ ነበር።ግንቦት ሃያ-አምስት።

በወሩ አንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ የጠራዉ ሠላማዊ የተቃዉሞ ሠልፍ ጎንደርና ደሴ ዉስጥ ተደረገ።የአደባባይ ተቃዉሞ ሠልፍ የማድረጉ ጥረት፥ ሙከራ፥ ዝግጅትም ቀጥሏል።የዚያኑ ያክል ተቃዋሚ ፖለቲከኞች እንደሚሉት በአባሎቻቸዉና በደጋፊዎቻቸዉ ላይ መንግሥት የሚፈፅመዉ እስራት እንግልትም አላባራም።

ግንቦትና ሰኔ፥-የኢትዮጵያንና የግብፅን የቃላት እንኪያ ሰላንታ እንዳሰሙን-ሐምሌ ተካቸዉ።

የአዉሮጳ ምክር ቤት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ባርባራ ሎኽቢኸር የመሩት የመልዕክተኞች ቡድን ኢትዮጵያን ጎብኝቶ ነበር።ሐምሌ።ቡድኑ ከመንግሥትና ከተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር ከተነጋገረ በሕዋላ እስረኞችን ለመጎብኘት ጠይቆ ተፈቅዶለት ነበር።ቃሊቲ ሲደርስ «ማንፈቅደለሕ» ተባለ።

የዘንድሮዉ ሐምሌ ለሙስሊሞች የቅዱስ ረመዳን ወር ነበር።የየመስጊዱ ተቃዉሞ ጩኸታቸዉ ግን አላባራም።፥ በተቃዉሞዉ ሰበብ ከፀጥታ አስከባሪዎች የሚደርስባቸዉ ወከባ እስራት አንዳዶች እንደሚሉት ዘረፋና ግፍም ብሶ ቀጥሏል።ለኮፈሌ፥ለኢዶ፥ለዋቤ፥ለቆሬ ከተሞች ደግሞ የዘንድሮዉ ረመዳን የአሳዝኝ ግድያ ወርም ነበር።

ሐምሌ ማብቂያ ፀጥታ አስከባሪዎች በበተሰበሰቡ ሙስሊሞች ላይ በከፈቱት ተኩስ ሲያንስ አስር ሲበዛ ሃያ-ስድስት ሰላማዊ ሰዎች ገድለዋል።ኢድ-አልፊጥር የፌስታ፥ ደስታ፥ ታላቅ ዕለት ነዉ።የአዲስ አበባ ሙስሊሞች የዘንድሮዉን ረመዳን የፈጠሩት፥ ኢድን ያከበሩት የከብት፥ የበግ፥ የዶሮ ደም አፍስሰዉ ሳይሆን በፖሊስ ቆመጥ የራሳቸዉን ደም አዝርተዉ ነበር።ሁለት ጋዜጠኞችም ታስረዉ ነበር።ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት የጋዜጠኞቹን መታሰር አዉግዟል።


በዓለም ላይ በሸሪዓ ሕግ የሚገዙ ሁለት ሐገራት አሉ።ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ።ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ በኢድ አልፊጥር ማግሥት እንዳሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢትዮጵያን በሸሪዓ ሕግ የምትገዛ ሰወስተኛ ሐገር ለማድረግ ይጥራሉ።

ዘንድሮ-ሰወስት ሚንስትሮች የተሻሩ፥ ከሰወስቱ አንዱ ከተከታዮቻቸዉ በሙስና የታሰሩበት፥ አዳዲስ ሚንስትሮች የተሾሙበት፥ ኢትዮጵያ ባለ-ሠወስት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ካቢኔ የሰየመችበትም ዓመት ነዉ።ማክሰኞ-ያበቃል።ነጋሽ መሐመድ ነኝ።መልካም አዲስ አመት።

ነጋሽ መሐመድ

Thousands of Ethiopian opposition activists demonstrate in Addis Ababa on June 2, 2013. The protests were the largest in the country since post-election violence in 2005, in which 200 people were killed and hundreds more arrested. The activists have vowed to press ahead with demonstrations calling for government reforms and the release of political prisoners. The demonstrations were organised by the newly-formed Blue Party opposition group. Government spokesman Bereket Simon said up to 4,000 people joined Sunday's demonstration, while some observers put the number at 10,000. AFP PHOTO/STRINGER (Photo credit should read STRINGER/AFP/Getty Images)
ተቃዉሞ ሠልፍምስል Stringer/AFP/Getty Images
Titel: Demo. in Addis Abeba Schlagwörter: Demo. blaue Partei, Äthiopien Autor: Y. G.Egziabher ( DW Correspondent Addis Abeba Datum: 02.06.2013
ምስል Y. G.Egziabher
Titel: Demo in Addis Abeba Schlagwörter: Demo. blaue Partei, Äthiopien Autor: Y. G.Egziabher ( DW Correspondent Addis Abeba) Datum: 02.06.2013
ተቃዉሞ ሠልፍምስል DW/Y. G.Egziabher
Addis Abeba, Äthiopien, Aufgenomen von unser Kori. ,Yohannes Gebereegziabher in Wahlurnen. Titel Wahlen in Addis Abebe Schlagworte Wahlurnen Datum 21 04 2013 Fotograf Gebereegziabher,Yohannes
ምርጫምስል Yohannes Gebereegziabher

ተክሌ የኋላ




















ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ