የ2 ቱ የሱዳን መንግሥታት ስምምነት30 ሐምሌ 2004ሰኞ፣ ሐምሌ 30 2004ሁለቱ የሱዳን መንግሥታት ፣ 2 ወር ገደማ ያህል ያካሄዱት የሰላም ድርድር ፣ አወንታዊ ውጤት እንደታየበት፤ ዋናው ሸምጋይ ፤ የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት ታቦ እምቤኪ አስታውቀዋል። አብዛኛው የአፍሪቃ ክፍል ፤ ከቅኝ አገዛዝ ከተላቀቀ ከ 50 ዓመት በላይ ቢሆንም የድንበር አካባቢ የካርታ ንድፍ ፤https://p.dw.com/p/15krUምስል Reutersማስታወቂያ በተለይ ደግሞ የከርሠ ምድር ሀብት መኖሩ ከተረጋገጠ፤ ለአምባጓሮ መጋበዙ አይቀሬ መስሎ መታየቱን ፣ የሱዳንና ደቡብ ሱዳን አለመግባባትም አንዱ ምክንያትይኸው መሆኑን ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ የላከው ዘገባ ያስረዳል። ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ ,ክሌ የኋላ ሂሩት መለሰ