የ19 አመቱ አትሌት መሀመድ አማን
ዓርብ፣ ግንቦት 2 2005ማስታወቂያ
የ19 አመቱ መሀመድ አማን ተወልዶ ያደገው በአርሲ ፤አሰላ ከተማ ነው። እሱ እንደሚለው የሩጫውን አለም እንደቀልድ ነው የተቀላቀለው። መሀመድ ዛሬ ሌሎች አይናቸውን ተክለው ሲሮጥ የሚከታተሉት አትሌት ለመሆን በቅቷል። መሀመድ እንደ በርካታ የኢትዮጵያ አትሌቶች ትውልዱ አርሲ አካባቢ ነው። ለብዙ አትሌቶች ስኬት የሆነው ሚስጥሩ ተግቶ መስራት ነው ይላል።
ወጣቱ በወጣቶች የኦሎሞኒክስ አትሌቲክስ ውድድር፣ በአለም ወጣቶች ሻምፒዎና ውድድሮች እና ሌሎችም የመካከፈል እና የማሸነፍ እድል ገጥሞታል። ዛሬ ደግሞ (ግንቦት 2፤ 2005) ዶሀ ላይ ጎልደን ሊግን በተካው ድያመንድ ሊግ በመባል በሚታወቀው እና እኢአ ከ2010 ጀምሮ በሚካሄደው ውድድር ይሳተፋል።
መሀመድ ስለ የአትሌቲክስ ህይወቱ ከዶይቸ ቬለ ጋ ያደርገውን ቆይታ የድምፅ ዘገባውን በመጫን መስማት ይችላሉ።
ልደት አበበ
ነጋሽ መሀመድ