የ 2 ቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ብይን
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 17 2004ማስታወቂያ
። ማርቲን ሺብዬና ዮሐን ፔርሶን በተባሉት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ በዛሬው ዕለት ፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ችሎት ያስተላለፈውን ብይን የተከታተለው ታደሰ እንግዳው ዘገባ ልኮልናል። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የስዊድን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አንደርስ ዮርለ መንግስታቸዉ ዜጎቹን በነፃ ለማስለቀቅ እንደሚጥር አስታውቀዋል ። ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት በምህፃሩ RSF ብይኑን ተችቷል ። ስለ ብይኑ የስዊድን ህዝብ አስተያየት ምን እንደሆነም የስቶክሆልሙን ዘጋቢያችንን አነጋግረናል ።
ታደሰ እንግዳው
ቴዎድሮስ ምህረቱ
ሉድገር ሻዶምስኪ
ተክሌ የኋላ
ሂሩት መለሰ