የፖሊስ የግድያ ርምጃ በቺካጎ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 21 2008ማስታወቂያ
ባለፈው የፈረንጆች የገና በአል ማግስት በኢሊኖይስ ግዛት ችካጎ ከተማ አንድ የ19 አመት ወጣትና የ55 አመት ወይዘሮ በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ተከትሎም የከተማዋ ከንቲባ ከስልጣናቸው እንዲለቁ የሚጠይቁ ሰልፈኞች በርክተዋል። ከንቲባ ራም ኢማኑኤል የሰልፈኞቹን ጥያቄ ወደጎን በመተው ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስተዳደራቸው በከተማዋ ፖሊስና በህብረተሰቡ መካከል የተፈጠረውን አለመተማመን ሊቀርፍ የሚችል አዲስ ፖሊሲ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ናትናኤል ወልዴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ