የፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ስብሰባ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 11 2008ማስታወቂያ
ኢህአዲግን ጨምሮ 9 የፖለቲካ ፓርቲዎችን በአባልነት ያቀፈው የጋራ ምክር ቤቱ ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በኦሮምያ እና በአማራ ክል በተፈጠሩ ብጥብጦች ለጠፋ ህይወት ሃዘኑን በመግለጽ አመፁን ጠሩ የተባሉ ህገ ወጥ ያሏቸው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል ። ከዚህ ሌላ በወቅቱ የደረሰው ጉዳት በገለልተኛ አካል እንዲጣራም አሳስቧል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከጋራ ምክር ቤቱ አባላት መካከል የቅንጅት ፓርቲ እና የመላ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ መሪዎችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሠ