1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎችና አዲሱ ዓመት

ሰኞ፣ መስከረም 3 2008

በአዲሱ ዓመት ሰላማዊ ትግላቸዉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ አድርገዉ እንደሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ።

https://p.dw.com/p/1GWJt
Karte Äthiopien englisch


የኢትዮጵያ ፊደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ «መድረክ» በአጭሩ ፤ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ « ኢራፓ» ሰማያዊ ፓርቲ፤ አንድነትና የመላዉ የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት «መኢአድ» አመራር አባላት ለዶቼ ቬለ በአዲሱ ዓመት ሰላማዊዉን የሕዝብ ንቅናቄ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉበት ተናግረዋል። ያለፈዉ ቁርሾ በብሔራዊ ዕርቅና መግባባት እንዲፈታ የትግል አቅጣጫዬ አድርጌ እንቀሳቀሳለሁ ሲል የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ «ኢራፓ » ገልፆአል። የሰማያዊ ፓርቲ ለቀመንበር በበኩላቸዉ ፓርቲያቸዉ በቅርቡ ጉባኤ ማካሄዱንና የካቢኔ አባላት የመሰየም ሂደት በቅርቡ እንደሚካሄድ ገልፀዋል።

ዮኃንስ ገብረግዚአብሄር


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ