የፖለቲካ ቀዉስ በየመን
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 27 2006ማስታወቂያ
ተቃዋሚዎቹ የሀገሪቱን ፓርላማ መግቢያ ጎዳናም አጥረዉ ይዘዉ መዉጫና መገበያያንም መዝጋታቸዉ ነዉ የተነገረዉ። ሰልፈኞቹ በጥያቄያቸዉ እነሱን የማይወክለዉ የጠቅላይ ሚንስትር የመሀመድ ባዚንዳዋ መንግሥት ከስልጣን ተወግዶ፤ በምትኩ አንድ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መንግሥት እንዲቋቋም ጠይቀዋል። ይህ ወዴት እንደሚያመራ የማይታወቀዉ የየመን ዉስጣዊ ዉዝግብ የተመድን እና የአዉሮጳን መንግሥታት እያሳሰበ መጥቶዋል። የዶይቸ ቬለዋ ኬርስትን ክኒፕ ስለየመን የፖለቲካ ቀዉስ ያጠናቀረችዉን ዘገባ ይልማ ኃይለሚካኤል እንዲህ ያቀርበዋል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ