1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬዚዳንት ጋውክ የእሥራኤል ጉብኝት፣

ሰኞ፣ ግንቦት 20 2004

ባለፈው መጋቢት ፣ ለርእሰ ብሔርነት የተመረጡት የቀድሞዋ ጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ (የምሥራቅ ጀርመን ዜጋ) አሁን የመላይቱ ጀርመን ፕሬዚዳንት ዮኣኺም ጋውክ፤ ለጥቂት ቀናት ጉብኝት ዛሬ እሥራኤል መግባታቸው ታውቋል።

https://p.dw.com/p/153dS
ምስል picture-alliance/dpa

ባለፈው መጋቢት ፣ ለርእሰ ብሔርነት የተመረጡት የቀድሞዋ ጀርመን ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ (የምሥራቅ ጀርመን ዜጋ) አሁን የመላይቱ ጀርመን ፕሬዚዳንት ዮኣኺም ጋውክ፤ ለጥቂት ቀናት ጉብኝት ዛሬ እሥራኤል ገብተዋል። የእሥራኤል ፕሬዚደንት ሺሞን ፔሬስ ይፋው ጉብኝት በሚጀምርበት በነገው ዕለት ጀርመናዊውን አቻቸውን ከተቀበሉ በኋላ፡ ሁለቱ መሪዎች የሆሎኮስት መታሰቢያ የሚገኝበትን ቫድ ያሼምን ባንድነት ይጎበኛሉ። ፕሬዚደንት ጋውክ በዚሁ ጉብኝታቸው ጀርመን ከእሥራኤል ጎን የመቆሟን መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚፈልጉ በእሥራኤል የጀርመን ኤምባሲ ቃል አቀባይ ገልጾዋል። ጀርመናዊው ፕሬዚደንት የፊታችን ሐሙስ ወደ ራማላህ በመሄድ ከፍልሥጤማውያኑ ራስ ገዝ መስተዳድር ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስ ጋ ይገናኛሉ። ስለ ፕሬዚዳንቱ የጉብኝት ዓላማና ስለሁለቱ አገሮች የጠበቀ ግንኙነት፣ በጀርመን የበርሊኑንና በእሥራኤል የሃይፋውን ዘጋቢዎቻችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ና ግርማ አሻግሬን በስልክ አነጋግረን ነበር።


ተክሌ የኋላ

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ግርማው አሻግሬ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ