1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪቃ ጉዞ ተቃውሞ ዘመቻ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 30 2007

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከኢትዮጵያ፣ከኬንያ እና ከአፍሪቃ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት የፊታችን ሀምሌ ወር ወደ አፍሪቃ መሄዳቸው የሰሞኑ ወሬ ነው።

https://p.dw.com/p/1Fu8i
Washington Supreme Court Entscheid über Obamacare PK Obama
ምስል Reuters/G. Cameron

[No title]

የኦባማን ወደ ኢትዮጵያ መሄድ የሰሙ ኢትዮጵያውያን አሜሪካዉያን ባለፈው ዓርብ በ«ኃይት ሀውስ» ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ተቃዋሚዎቹ፤ ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ጉዞዋቸውን እንዲሰርዙ የሚያሳስብ ደብዳቤ እና ከህዝብ የተሰበሰበ ፊርሚያ ለ«ኃይት ሀውስ» አስገብተዋል። ይህም ተቃውሞ እንደሚቀጥል ገልፀዋል። ላስገባችሁት ደብዳቤ ምላሽ አገኛችሁ ወይ? እና መሰል ጥያቄዎችን ለዋሽንግተን ዲሲ ግብረ ሀይል አስተባባሪ አመራር አባል እና ሌሎች የሰልፍ ተሳታፊዎችን በማነጋገር፤ የዋሽንግተን ዲሲ መክብብ ሸዋ የዘገበው።

መክብብ ሸዋ

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ