1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬስ ነፃነት ማሽቶልቆል

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 12 2008

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የ180 ሃገራትን የፕሬስ ነጻነት ደረጃ በዘረዘረበት ዘገባው እንደጠቆመው የፕሬስ ነፃነት በ2015 በተለይ በአውሮጳ ህብረትና በባልካን ሃገራት ባልተጠበቀ ሁኔታ በእጅጉ ተገድቧል ።

https://p.dw.com/p/1IZ9D
Symbolbild Pressefreiheit
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]



በጎርጎሮሳዊው 2015 በዓለም ዙሪያ የፕሬስ ነፃነት ማሽቆልቆሉን ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተባለው የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት አስታወቀ ። ድርጅቱ እንዳለው ባለፈው ዓመት ነፃ መረጃን በሚያስተላልፉ ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በሁሉም አካባቢዎች ጨምሯል ።ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የ180 ሃገራትን የፕሬስ ነጻነት ደረጃ በዘረዘረበት ዘገባው እንደጠቆመው የፕሬስ ነፃነት በ2015 በተለይ በአውሮጳ ህብረትና በባልካን ሃገራት ባልተጠበቀ ሁኔታ በእጅጉ ተገድቧል ።በድርጅቱ መዘርዝር የፕሬስ ነጻነት ደረጃቸው ከቀነሰው የአውሮጳ ሃገራት መካከል አንዷ ጀርመን ናት ። ስለ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የ2015 ዓመታዊ ዘገባና ጀርመን ስለተሰጣት ደረጃ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ