የፓን አፍሪቃ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉባኤ
ዓርብ፣ ኅዳር 20 2006ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ላይ ለተካሄደዉና ዛሬ ለተጠናቀቀዉ የመላዉ አፍሪቃ የንግድ እና ባለኢንዱስትሪዎችምክር ቤት ጉባኤዉ ይህን ያመለከቱት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የእርስ በርስ ግብይቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባዉም አሳስበዋል። ጉባኤዉ የአፍሪቃ ሃገራት ምርቶቻቸዉን እንዴት አቀናብረዉ ወደዉጭ ቢልኩ ገቢያቸዉን ማጠናከር ይችላሉ በሚለዉ ላይም ተነጋግሯል። የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ ሙሉ ሰሎሞን ኢትዮጵያ ምርቶቿን ከአፍሪቃ ዉጭ ለመላክ ገበያ አለማጣቷን በማመልከት፤ የጥራት ደረጃን ጨምሮ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ግን መኖራቸዉን አመልክተዋል። ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ
ሸዋዬ ለገሠ