የፓሪሱ ጥቃትና የዓለም ሠላም
ሰኞ፣ ጥር 4 2007ማስታወቂያ
«እስልምና ተራ መሆኑን እንደ ካቶሊካዊነት አምኖ እስኪቀበል ድረስ« ብሎ ነበር የሻርሊ ኤብዱ መፅሄት ዋና አዘጋጅ ፤ ስቴፋን ሻርል ቦንዬ የዛሬ ሁለት ዓመት ግድም፤ «እንቀጥልበታለን።» እሱና ባልደረቦቹ በዚያች ምፅታዊ መፅሄታቸዉ እስልምናን መተቸት፤ ማኪያኪያስ፤ ማንቋሸሻቸዉን ቀጠሉ። ሮብ ግን ተገደሉ። ፓሪስ ተሸበረች። ዓለም ደነገጠ። ግድያ፤ ሽብሩን አወገዘ። አዘነም፤ብዙዉ «እኔም ሻርሊ ኤብዶ ነኝ» አለ። ሌሎች ግን «ፍቅር ያሸንፋል።» ግድያ ሽብሩን አስታከን ዳራዉን፤ የድንጋጤ፤ ዉግዘት ግመት እንድምታዉን ከብራስልሱ ወኪላችን ከገበያዉ ንጉሴ ጋር ባደረግነዉ አጭር ዉይይትእንቃኛለን። ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ