የፓሪሱ ሽብርና በየመን አል ቃኢዳ
ሐሙስ፣ ጥር 7 2007ማስታወቂያ
ባለፈዉ ሳምንት ፓሪስ-ፈረንሳይ ዉስጥ አስራ-ሰባት ሰዎች ለተገደሉበት የሽብር ጥቃት በየመን የዓለም አቀፉ አሸባሪ ቡድን የአል ቃኢዳ ቅርንጫፍ ሐላፊነቱን መዉሰዱን አንዳድ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።ሰነዓ-የመን የሚገኘዉ ተባባሪ ዘጋቢያችን ግሩም ተክለ ሐይማኖት እንደሚለዉ ግን ለፓሪሱ ጥቃት ሐላፊነቱን የወሰደዉ የዓረቢያ አል-ቃኢዳ የተሰኘዉ ቡድን እንጂ የየመኑ አይደለም።ያም ሆኖ ፤ ግሩም እንደሚለዉ የመን የመሸገዉ የአል-ቃኢዳ ሐይል ከየመን አልፎ ሌሎች አካባቢዎችን የማጥቃት አቅም አለዉ።ግሩም ተክለ ኃይማኖትን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።
ግሩም ተክለ ሐይማኖት
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ