የፎቶ ስብስቦቿን በኒው ዮርክ የምታስገመግመው ወጣት
ዓርብ፣ መጋቢት 16 2008ማስታወቂያ
ከተለያየ ሀገር የተወዳደሩ ፎቶ አንሺዎች ተገኝተው ስራዎቻቸውን በተለያዩ ባለሙያዎች የሚያስገመግሙበት አራተኛው ዓመታዊ የኒው ዮርክ «ፖርትፎሊዮ ሪቪው» መጋቢት 24 እና 25 ቀን 2008ዓም ኒው ዮርክ ላይ ይካሄዳል። አዘጋጁ ደግሞ የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ነው።
በዚህ ዝግጅት የፎቶ ስራዎቻቸውን ለማስገምገም እድሜያቸው ከ 21 ዓመት በላይ የሆኑ ፎቶ አንሺዎች ተወዳድረዋል። የ 22 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ኢየሩሳሌም አዱኛ ከተመራጮቹ አንዷ ናት። ወጣቷ በስድስት ቀናት የኒው ዮርክ ቆይታዋ ፎቶዎቿን የምታቀርብበት ሌላ መድረክ ወይም ወጪዎቿን ለመሸፈን የሚተባበሯት አካል ለማፈላለግ ትጥራለች። ወጣቷ ፎቶ ማንሳት ከጀመረች ሶስት አመት ጊዜ የሆናት ሲሆን፤ አጠናክራ ከጀመረች ገና አንድ ዓመት ተኩል ሆናት። ይህንንም የተማረችውም፤ አጫጭር ኮርሶች በመውሰድ እንደሆነ ትናገራለች። ሶስት የተለያዩ የሙያ ዘርፎችን የዳሰሰችው እየሩሳሌም በመጨረሻም ወደ ፎቶ ማንሳት አድልታለች። ወደፊትም በዚህ የመቀጠል ዓላማ ነው ያላት።
ኢየሩሳሌም አዱኛ ኒው ዮርክ ስለምታቀርባቸው የፎቶ ስብስቦቿ እና ሥራዋ ያጫወተችንን በድምጽ ያገኙታል።
ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ