የፎልክስ ቫገን የመኪና ኩባንያ ቅሌት
ማክሰኞ፣ መስከረም 11 2008ማስታወቂያ
ይህ ውሳኔ የተወሰደው የዩኤስ አሜሪካ የተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ መስሪያ ቤት ፎልክስ ቫገን የመኪና አምራች ኩባንያ ለገበያ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች የሚተፉትን ከባቢ አየርን የሚጎዳውን የጢስ መጠን በሶፍትዌር አማካኝነት ዝቅ የማድረግ የማጭበርበር ተግባር ፈጽሞዋል ሲል ካጋለጠ በኋላ ነው። ኩባንያዉም ስህተት መስራቱን አምኖ ይቅርታ ጠይቋል። የዩኤስ አሜሪካ የከባቢ ጥበቃ ጉዳይ ባለስልጣን መስርያ ቤት ይፋ እንዳደረገዉ ፎልክስ ቫገን የተሽከርካሪ ኩባንያ 482 ሺህ ተሽከርካሪዎችን በማጭበርበር ለገበያ አቅርቦአል። በሌላ በኩል ድርጅቱ በዓለም ዙርያ 11 ሚሊዮን በዚሁ መልክ በናፍጣ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ኩባንያዉ ማቅረቡ ነዉ የተመለከተዉ። ዬኤስ አሜሪካ ፎልክስ ቫገን የመኪና አምራች ኩባንያ ላይ የጣለችዉን እገዳ ተከትሎ ፈረንሳይ ኢጣልያ ብሪታንያ ስዊጠርላንድ ደቡብ ኮርያ እና አዉስትራልያ ነገሩ በፍጥነት እንዲጣራ ጠይቀዋል። የዩኤስ አሜሪካዉ ዘጋብያችን አጠር ያለ ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ