1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍርድ ቤቱ ዉሳኔና ተቃዉሞዉ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2005

ከተፈረደባቸዉ ሁለቱ በቅርቡ የተዋሐዱት የኦሮሞ ሕዝብ ብሄራዊ ኮንግረስና የኦሮሞ ፌደራሊስቲ ፓርቲዎች ባለሥልጣናት ነበሩ።የተዋሐደዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ ፕሬዝዳት ዶክተር መረራ ጉዲና ቅጣቱን በሰላማዊና ሕጋዊ ትግል የሚያምኑ ፖለቲከኞችና ወጣቶችን ለማስበርገግ ያለመ ብለዉታል።

https://p.dw.com/p/170UW
Eine Statue der Justitia, Göttin der Justiz und der Gerechtigkeit, steht auf dem Gerechtigkeitsbrunnen auf dem Frankfurter Römerberg und hält eine Waage mit zwei Waagschalen in der Hand, fotografiert am 15.02.2008. Foto: Wolfram Steinberg +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/dpa


የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሁለት የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ ባለሥልጣናት እና በሰባት ተባባሪዎቻቸዉ ላይ ያሳለፈዉን የቅጣት ዉሳኔ የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ አጣጥሎ ነቀፈዉ።ትናንት ያስቻለዉ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኦነግ አባላት ያላቸዉን ዘጠኙን ተከሳሾች ከሰወስት እስከ አስራ-ሰወስት ዓመታት በሚደርስ እስራት ቀጥቷቸዋል።ከተፈረደባቸዉ ሁለቱ በቅርቡ የተዋሐዱት የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስና የኦሮሞ ፌደራሊስቲ ፓርቲዎች ባለሥልጣናት ነበሩ።የተዋሐደዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ፓርቲ ፕሬዝዳት ዶክተር መረራ ጉዲና ቅጣቱን በሰላማዊና ሕጋዊ ትግል የሚያምኑ ፖለቲከኞችና ወጣቶችን ለማስበርገግ ያለመ ብለዉታል።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ