የፍልስጤም ሰንደቅ ዓላማ በአዲስ አበባ17 ኅዳር 2008ዓርብ፣ ኅዳር 17 2008የፍልስጤም ሰንደቅ ዓላማ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪቃ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA)ቅጥር ግቢ ውስጥ መውለብለብ ጀምሯል።https://p.dw.com/p/1HDjvምስል DW/G. Tedlaማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio ይህም በተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ መሠረት የተከናወነ ሲሆን በስርዓቱ ላይ በርካታ የውጭ እና የሀገር ውስጥ አምባሳደሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የልማት ተቋማት ተጠሪዎች ተገኝተዋል። በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ የተገኘው የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ ልኮልናል። ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ልደት አበበ አርያም ተክሌ