የፊፋ አዲስ ፕሬዝዳንት ምርጫ ና ማሻሻያዎች
ዓርብ፣ የካቲት 18 2008ማስታወቂያ
ዓለም ዓቀፉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ፊፋ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ሴፕ ብላተርን ለመተካት ዛሬ ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ የስዊሱ ጊያኒ አንፋንቲኖ አብላጫ ድምፅ ቢያገኙም ለማሸነፍ የሚያበቃቸውን ሁለት ሶስተኛ ድምፅ አላሟሉም ። የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ደቡብ አፍሪቃዊው እጩ ራሳቸውን ከምርጫው በማግለላቸው ለፊፋ ፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት አራት እጩዎች ብቻ ነበሩ ። ፊፋ ከምርጫው በፊት ባካሄደው ጉባኤ መጠነ ሰፊ የውስጥ አሰራር ማሻሻያዎችን አጽድቋል ። እነዚህ ማሻሻያዎችም በሚቀጥሉት 60 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተገልጿል ። አዲሱ የፊፋ ፕሬዝዳንት የድርጅቱን ገፅታ የመቀየር ከባድ ሃላፊነት ይጠብቃቸዋል ። ስለ አዲሱ የፊፋ ፕሬዝዳንት ምርጫ የስፖርት ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ