1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፊልም ዳይሬክተር አዳነች አድማሱ

እሑድ፣ ነሐሴ 15 2008

አዳነች አድማሱ በኢትዮጵያ በፊልሙ ስራ ዘርፍ ከተሰማሩት ጥቂት ሴቶች አንዷ ናት። ባለፉት 10 ዓመታት ዘጋቢ ፊልሞች፣ ማስታወቂያዎችን ፣ የአመለካከት ለውጥ የሚያመጡ ህብረተሰቡን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ድራማዎችን በመምራት፣ ድምፅ አልባ ለሆኑት ድምፅ ሰጥታለች።

https://p.dw.com/p/1JmUj
Regisseurin Adanech Admasu Fesha
ምስል Adanech Admasu

የፊልም ዳይሬክተር አዳነች አድማሱ

አዳነች አዘውትራ በኢትዮጵያ በትምህርቱ እና በጤናው ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ « ዲ ኬ ቲ»፡ «ዩኒሴፍ»፡ « ኦክስፋም»፡ « ዋተር ኤድ»፡ « አውስትራሊያነ ዴቨሎፕመንት ክኦፐሬሽን»፡ን ለመሳሰሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰርታለች። አዳነች ከሰራቻቸው ፊልሞች መካከል ያላቻ ጋብቻ እና የቤት ምስሶ የሚጠቀሱ ሲሆን፡ እጎአ በ2005 ዓም «ያላቻ ጋብቻ » ለተባለው ፊልሟ በለንደን በተካሄደው የ« ዋን ዎርልድ ሚድያ አዋርድስ » ስነ ስርዓት ላይ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች።

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ