1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈርገሰኑ የዳኞች ሸንጎ ብይንና የቀጠለዉ ተቃውሞ

ረቡዕ፣ ኅዳር 17 2007

ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር መግቢያ ላይ ማይክል ብራውን የተባለው አንዳች የመከላከያ መሣሪያ ያልያዘ የ 18 ዓመት ወጣት ፣ዳረን ዊልሰን የተሰኘው ነጭ ፖሊስ በተደጋጋሚ ጥይት ተኩሶ መግደሉ ብዙ የተባለለት ጉዳይ ነው።

https://p.dw.com/p/1DuEE
USA Lage in Ferguson 21. August
ምስል DW/M. Soric

ከዚያን ጊዜ አንስቶም በቋፍ ላይ የቆየችው ሚዙሪ በተሰኘው ፌደራል ክፍለ ሀገር የምትገኘው ከተማ ፣ ፈርግሰን ፣ ትናንት የዳኞች ጉባዔ ገዳዩን በነጻ ካሰናበተ ወዲህ ከተማይቱ በቁጣ በገነፈሉ የተቃውሞ ሰልፈኞች ታምሳለች። ተቃውሞ በአገሪቱ በመላ በ 170 ከተሞችም ተካሂዷል።

USA Proteste in Ferguson
ምስል picture-alliance/dpa

በቁጥር እጅግ የሚያመዝኑ አፍሪቃውያን አሜሪካውያን ፣ በብዙው የአስተዳደር ክፍል ደግሞ ጥቂቶች ነጮች የበላይነቱን በያዙባት ከተማ በፈርገሰን ፤ ጥቁሩ የ 18 ዓመቱ ወጣት ማይክል ብራውን አምና በነሐሴ ከተገደለ ወዲህ፤ በዩናይትድ ስቴትስ ፈታ ያላለውን የዘር ልዩነት እንዲያገረሽና በአፍሪቃውያን አሜሪካውያንና ማህበረሰብና በዩናይትድ ስቴትስ ፖሊስ መካከል ያለውን ያልሠመረ ግንኙነት ይበልጥ እንዲሻክር ሳያደርግ እንዳልቀረ ነው የሚነገረው። አፍሪቃውያን አሜሪካውያን፣ አድልዎ ተፈጸመብን የሚል ስሜት እንዲያድርባቸው ፣ በተደጋጋሚ የተፈጸሙ ተመሳሳይ ድርጊቶች እንደሚገፋፏቸው የሚናገሩም አሉ። እ ጎ አ መጋቢት 3 ቀን 1991 ዓ ም፤ ሎስ ኤንጀለስ ላይ ፖሊሶች፣ ሮድኒ ኪንግ የተባለውን ጥቁር አሜሪካዊ ፤ አልኮል መጠጥ ጠጥተህ ከሚገባ በላይ በፍጥነት ነድተሃል በሚል ሰበብ፣ ከአውቶሞቢል እንዲወርድ አስገድደው ጎዳና ላይ ክፉኛ መደብደባቸው ፤ መቀጥቀጣቸው በአንድ አማተር ፊልም አንሺ በደብቅ ተቀርጾ መታየቱና ፤ በዩናይትድ ስቴትስና በሌላውም የዓለም ክፍል የፖሊሶቹን ጭካኔ ያስመሰከረ እንደነበረ የሚታወስ ነው።ደብድበው ፤ በኀላፊነት የተጠየቁት 2 የፖሊስ መኮንኖች ከአንድ ዓመት በኋላ በነጻ መለቀቃቸው ብርቱ ሁከት አስከትሎ እንደነበረም አይዘነጋም።

Ausschreitungen in Ferguson 24.11.2014
ምስል Reuters/Jim Young

በፈርገሰን ትክክለኛ ፍትሕ አልተገኘም የሚሉ ወገኖች ፣ በኒውዮርክ ፤ ሎስ አንጀለስ፣ አትላንታ ፤ ኦክላንድ ፣ ሳን ፍርንሲስኮና በአጠቃላይ ከ 170 በማያንሱ ከተሞች የተለያዩ የተቃውሞ ስልፎች አሳይተዋል። በሚዙሪ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ፕሮፌሰር ጆይስ ማስሔበን ፣ በዩንይትድ ስቴትስ ሕግ ሁለት ዓይነት አያያዝ ፤ የመደብ ልዩነት ሥርዓት ነው ወይ የሚንጸባረቀው የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ

«የሁለት መደብ ሥርዓት መኖሩ የተረጋገጠ ነው። ነገር ግን ፤ በቀለም ልዩነት የሚታይ አይደለም። በገንዘብ አቅም የሚለካ ነው። በገንዘብ ኤይል ጥሩ ጠበቃ ማቆም የሚችል፤ የተሻለ ግልጋሎት በሚሰጥባቸው አካባቢዎች መኖር የሚችል፤ የተሻለ የትምህርት ዕድል የሚያገኝ፤ የተሻለ im,ሥtra ዕድል ማግኘት ይችላል። ይህ ያልተስተካከል ገንዘብ የማግኛው ምንጭና ፣ የትምህርቱ ሥርዓት ነው የችግሩ ፤ የውዝግቡ ሥረ መሠረት።»

የአሜሪካ ፖሊስ የወረሰው የዘረኛነት መንፈስ ይኖር ይሆን ሌላው የቀረበላቸው ጥያቄ ነበር --አጭር መልሳቸው--

«ረኛነት ከቶውንም ይወረሳል አልልም። ሰዎች እንዲያ እንዲሆኑ ሠልጥነው ይሆናል፤ ወይም በሌላ የከተማ ክፍል ከሚኖሩ ሰዎች ጋር የመተዋወቅ ዕድልም ሆነ አጋጣሚ አላገኙ ይሆናል። በፌርገሰን ና በሌሎች የሴንት ልዊስ ከተማ ክፍሎች ዋናው ችግር ፣ ፖሊሶቹ ከሞላ ጎድል ነጮች በመሆናቸው ነው።»

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ