1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳይ አዲሱ ፕሬዝዳንት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 7 2004

አዲሱ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦላንድ ከጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ከወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ጋር ለመነጋገር ወደ በርሊን ለመምጣት የጀመሩት ጉዞ በአዉሮፕላን አደጋ ምክንያት ታጎለ።ኦላድን የተሳፈሩበት አዉሮፕላን ከፓሪስ አዉሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ በመብረቅ ተመትቷል።

https://p.dw.com/p/14w7W
ምስል Reuters

አዲሱ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦላንድ ከጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ከወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ጋር ለመነጋገር ወደ በርሊን ለመምጣት የጀመሩት ጉዞ በአዉሮፕላን አደጋ ምክንያት ታጎለ።ኦላድ የተሳፈሩበት አዉሮፕላን ከፓሪስ አዉሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ በመብረቅ ተመትቷል።ፕሬዝዳንቱና አብረዋቸዉ ያሉት ባለሥልጣኖቻቸዉ ግን የደረሰባቸዉ ጉዳት የለም። የተመታዉ አዉሮፕላን ወዲያዉ አርፎ፥ ኦላንድና ባለሥልጣኖቻቸዉ በሌላ አዉሮፕላን ወደ በርሊን ጉዞ ጀምረዋል።ኦላንድ በርሊን ዉስጥ ከጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ከወይዘሮ አንጌላ ሜርክል ጋር የሚያደርጉት ዉይይት በተለይ በአዉሮጳ የቁጠባ መርሕ ላይ ባላቸዉ የተለያየ አቋም ላይ ያተኩራል ተብሎ ይጠበቃል።ፕሬዝዳት ኦላንድ ወደ በርሊን የሚመጡት ዛሬ በተጠቅላይ ሚንስትርነት የሾሟቸዉን ዠ ማርክ ኤሮን አስከትለዉ ነዉ።ኤሮ ጀርመንኛ አቀላጥፈዉ የሚናገሩ የቀድሞ የጀርመንኛ መምሕር ነበሩ።የኤሮ የጀርመንኛ ዕዉቀት የሁለቱን መንግሥታት ልዩነት ለማጥበብ ይረዳል የሚል እምነት አሳድሯል።ኦላንድ የፕሬዝዳንትነቱን ሥልጣን ከቀድሞዉ ፕሬዝዳት ከኒላ ሳርኮዚ በይፋ የተረከቡት ዛሬ ነዉ።የሥልጣን ርክክቡን በተመለከተ የፓሯሷ ወኪላችን ሐይማኖት ጥሩነሕ በስልክ አነጋግሬያት ነበር።

ሐይማኖት ጥሩነሕ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ