1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤትና የመን

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 7 2007

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት፣ የመን ውስጥ በሁቲ አማጽያን ላይ የጦር መሳሪያ እገዳ እንዲደረግ ወስኗል። በውጊያ ላይ የሚገኙት ሁለቱም ተጻራሪ ኃይሎች ለየመን ዕርቀ-ሰላም ይወርድላት ዘንድ ተገናኝተው እንዲወያዩም ተጠይቀዋል።ከአምስቱ

https://p.dw.com/p/1F92q
ምስል REUTERS/L. Jackson

ቋሚ የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት አባላት መካከል ሩሲያ ድምጽ-ተዓቅቦ ከማድረጓ በስተቀር የተቀሩት ዐራቱና 10 ተለዋዋጭ አባል ሃገራት በአጠቃላይ 14 አገሮች ውሳኔውን ድምፅ በመስጠት ደግፈውታል። በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት፣ ከ 15 ቱ አባል ሀገራት ድምፅ በመስጠት ውሳኔውን ያጸደቁት 13 ናቸው ተብሎ መጠቀሱ መጀመሪያ ላይ ትንሽ ግር የሚል ሁኔታን ፈጥሮ ነበር።

የወቅቱ የፀጥታው ም/ቤት ሊቀመንበር ዮርዳኖስ ስትሆን፤ ድምፅ ቆጠራውን በተመለከተ እንዲህ ተነገረ---

«የድምፅ ቆጠራው ውጤት እንደሚከተለው ነው። ድምፅ የሰጡት 13 ናቸው።»

በወቅቱ የም/ቤቱ ሊቀመንበር ዮርዳኖስ በኩል ስለድምፅ አሰጣጡ የተነገረው ግራ- አጋቢ ነበር። ውሳኔውን ለማሳለፍ ብዙ ውጣ ውረድ ነበረ የተካሄደው።ዮርዳኖስም ፤ ሩሲያም በየበኩላቸው ረቂቅ ውssኣኔy አቅርበው ነበረ። ምናልባትም ሩሲያ ድምጽን በደምጭጽ የመሻር መብቷ (ቪቶ) ውድቅ ታደርገው ይሆንል የሚል ሥጋትም አሳድሮ ነበር።

Jemen Luftschläge auf Sanaa
ምስል Reuters/K. Abdullah

መጨረሻ ላይ ግን ፤ በኃይል ርምጃና ሁከት ለምትታመሰው ሀገር ይበጃል የተባለው ውሳኔ በ 14 ድምጽ ድጋፍና በሩሲያ ድምጸ -ተዓቅቦ ሊጸድቅ ችሏል።

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት፣ ባሳለፈው ውሳኔ፣ ሁቲ አማጽያንን ማስጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን፤ ካገር ለኮበለሉት ህጋዊው ፕሬዚዳንት ሃዲ ፣ ድጋፍ መስጠቱን ነው ያረጋገጠው። የውሳኔው ተቀዳሚ ዓላማ ፤ ለሁቱ አማጽያን ጦር መሳሪያ እንዳይሰጣቸው እገዳ ማስተዋወቅ ነው።እገዳው አህመድ ዓሊ ሳሌህን ማለትም የቀድሞውን የየመን ፕሬዚዳንት አብደላ ሳሌህን ልጅም ይመለከታል። አህመድ ዓሊ ሳሌህ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በኩል ስማቸው በእኩይነት መዝገብ ላይ ሠፍሯል። በሁለቱ ታፋላሚ ወገኞች ተወካዮችም ላይ የጉዞ እገዳ ከመደረጉም፤ በውጭ ያላቸው ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል። በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ ሳማንታ ፓዎር----

Huthi-Protest gegen saudi-arabische Luftangriffe in Sanaa
ምስል picture-alliance/dpa

«በዓለም ዙሪያ ያላቸው ንብረት እንዳይንቀሳቀስ፤ ካገር አገር እንዳይዘዋወሩ እንዲሁም፣የተጣለው የጦር መሳሪያ እገዳ የሚያሳየው፤ ይህ ም/ቤት ፣ ዕርቀ- ሰላም እንዳይወርድ እንቅፋት በሚሆኑት ላይ ሁሉ እርምጃ እንደሚወስድ ነው።»

በጸጥታ ጥበቃው ም/ቤት ንግግር ካሰሙት መካከል በዛ ያሉት፤ ውዝግቡ፤ ለአሸባሪ ቡድኖች መነገድ ጠራጊ ነው የሆነላቸው። እ ጎ አ ከመጋቢት ወር ማለቂያ አንስቶ፤ በስዑዲ ዐረቢያ መሪነት በሁቱ አማጽያን ላይ የሚካሄደው የአየር ኃይል ድብደባ፣ ሁኔታውን እንዲሻሻል አላደረገም ፤ ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቃና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን፤ እንዲህ ነበረ ያስጠነቀቁት።---

«ሁቲዎች በጦር ኃይል ወደፊት ከገሠገሡ ወዲህ፤ ሁኔታው የዐረብ መንግሥታት ማሕበር ወታደራዊ ርምጃ ይበልጥ ነው የተባባሰው።»

በገጠር የሚኖረው ሕዝብ፤ ለሕልውና በመጣጣር ላይ ይገኛል። ሀኪም ቤቶችና ት/ቤቶች፤ መዘጋት ነው ግድ ነው የሆነባቸው። አንዳንዶች እንዲያውም ፣ የጥቃቱ ቀጥተኛ ሰለባዎች ነው የሆኑት።

«ሆስፒታሎችና ት/ቤቶች በመዘጋት ላይ ናቸው። እንዳንዶች እንዲያውም፤ በቀጥታ የውጊያው ዒላማዎች ነው የሆኑት።»

Jemen Sanaa Luftschläge Saudi Arabien Luftabwehr
ምስል picture-alliance/dpa/Sinan Yiter / Anadolu Agency

ሩሲያ፣ ቀደም ሲል እንደተገለጸው ፣ድምጸ-ተዓቅቦ አድርጋለች። ገንቢ የሆኑ የመፍትኄ ሐሳቦቿ ትኩረት እንዳልተሰጣቸው በመጥቀስ ነቀፌታ ብጤ የሰነዘሩት በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ ተጠሪ፤ ቪታሊ ቹርኪን ናቸው።

«የአሁኑ ውሳኔ ብዙ ጉዳዮችን ያካተተ አይደለም በማለት በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ ተጠሪ ነቅፈዋል። እርሳቸው አንደተገነዘቡት ውሳኔው በማጽያኑና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሳሌህ አንጃ ላይ ያነጣጠረ ነው። የመንግሥት ወታደሮችም ተኩስ ለማቆም መገደድ ይኖርባቸዋል። »

ቪታሊ ሹርኪን

«ሁሉም ወገን የሚያውቀ ነው። የመን በአሁኑ ጊዜ በጦር መሣሪያ ብዛት የተጥለቀለቀች ሀገር ሆናለች»

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ