የጳጳስ ማርጎት ኬስማን ሰለጣን መልቀቅ
ሐሙስ፣ የካቲት 18 2002ማስታወቂያ
የጀርመን ፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ምክር ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ሊቀ መንበር ጳጳስ ማርጎት ኬስማን ጠጥተው መኪና ሲነዱ በመያዛቸው ትናንት ከሰዓት በይፋ የጵጵስና ስልጣናቸውን ለቀዋል ። የ51ዓመቷ ኬስማን ከዚህ ዓመት ከጥቅምት ወር አንስቶ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን የጀርመን ፕሮቴስታንት ምክር ቤት ሀላፊነታቸውንና የታህታይ ሳክሰኒ የጵጵስና ስልጣናቸውን ነው የለቀቁት
የኬስማን ከስራ መሰናበት የጀርመን ፖለቲከኞችንና የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን መሪዎችን አሳዝኗል ። ህዝቡ በበኩሉ የተለያየ አስተያየት እየሰጠ ነው ። ለመሆኑ ኬስማን ማናቸው ?