የጫት ጉዳትና ጥቅሞች በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 7 2008ማስታወቂያ
ጫት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ጥቅምና በጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በቅጡ እንዲጤን ስለ ጫት ጥናታዊ ጽሁፎች ያቀረቡ ምሁራን አሳሰቡ ። «ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ» የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ባዘጋጀው አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት ቀናት በተካሄደው ዐውደ ጥናት ላይ የጫት ኤኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ጠቀሜታ ተዘርዝሯል። በአንፃሩ ጫት ሱሰኝነትን ጨምሮ የሚያስከትላቸው የተለያዩ የጤና ችግሮችም ተነስተዋል። በዐውደ ጥናቱ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስለጫት ጥናታዊ ፅሁፎችን ያቀረቡ ምሁራንን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ