የጥበብ ፈርጦች ይታሰቡ!
ሐሙስ፣ ሰኔ 2 2003ማስታወቂያ
የአገር ባህሉ ፈርጥ የፉከራና የሽለላዉ አባት የመሲንቆዉ ጌታ የባህል ሙዚቃዉ አንባሳደር ይርጋ ዱባለ፣ በመሲንቆ ጭራ አገር አስከባሪ፣ በመረዋ ድምጹ ስሜት የሚያረካ፣ ስሜት የሚያነቃ፣ ጭንቀት የሚያስረሳ፣ አገር ተላላ ነዉ እያለ ዳመሉ ማሲንቆ ሲመታ ሲያቅራራ በቃሉ ነፍስ የሚዘራበት የፈራዉን ሁሉ፣፡የሚቀሰቅሰዉ የተኛዉን ሁሉ ! ተብሎላቸዋል፣ የሰማንያ አንድ አመቱ አዛዉንት ይርጋ ዱባለ በሰማንያ አንድ አመታቸዉ ከዚህ አመት ቢለዩንም ስራቸዉ ስማቸዉ ከመቃብር በላይ ዉሉአል። ሊቀ መኳስ ይርጋ ጉባለን በማሰብ የባህል ሙዚቃችን እንዲያብብ ለትዉልድም ታሪክን ባህልን ለማስተላለፍ ምን እየተደረገ ነዉ? በለቱ ቅንብራችን የምናየዉ ነዉ ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
ሸዋዪ ለገሰ