የጥበብ እመቤት አርቲስት አርቲስት ዘነበች ታደሰ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 22 1999ማስታወቂያ
ለበርካታ አመታት ከመድረክ ተለይታ የማታዉቅ አንጋፋዋ የጥበብ እመቤት አርቲስት ዘነበች ታደሰ ዘንድሮ የአዲስ አበባዉ ብሄራዊ ትያትር ሃምሳኛ አመት የምስረታ በአሉን ባከበረበት ወቅት ሎሚ ብወረዉር የተሰኘዉን ዜማዋን አቅርባለች። በብዙዎቻችን ዘንድ ጭራቀረሽ በሚለዉ በቅጽል ስሟ የምናቃት አርቲስት ዘነበች በድንገተኛ ህመም መጋቢት ሰባት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። በድንገት ከዚህ የተለየችዉ የአርቲስት ዘነበች ታደሰ የአርባ ቀን መታሰያ ወዳኦችዋ አፍቃሪዎችዋ ዘመዶችዋ በተገኙበት ታስቦ ዉሎአል። ስለ አንጋፋዋን የጥበብ እመቤት ዘነበች ታደሰ ከደራሲ ተዉኔት እና ገጣሚ አያልነህ ሙላት ጋር እናወሳለን