የጡረተኞች ቅሬታ በአዋሳ
ዓርብ፣ የካቲት 25 2003ማስታወቂያ
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአቤቱታ አቅራቢዎቹ ተወካይ፤ 350 የምንሆን ጡረተኞች ላለፉት ስምንት አመታት ጡረታ ታግዶብን ከነቤተሰባችን አደጋ ውስጥ ነን ብለዋል።ከልጅነታችን ጀምሮ ያጠራቀምነው የራሳችን ገንዘብ እንጂ ከመንግስት ካዝና እንዲከፈለን አልጠየቀንም ያሉት አቤቱታ አቅራቢዎች በወንጀል ተጠይቀን ተለቀናል። መንግስትም የጡረታ አዋጁን ስላሻሻለ ሊታገድብን አይገባም ሲሉ ይገልጻሉ። አቶ አዳነ ደበበ በማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን የደቡብ ሪጅን የመዋጮ ገቢና አስተባባሪ ውሳኔ ክፍያ የሥራ ሂደት ባለቤት የሚሉት ከ20 ዓመት በታች ያገለገሉና 3 ዓመት በእስር የቆዩትን አዋጁ አያካትትም ነው።
መሳይ መኮንን
ሂሩት መለሰ