1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ኃይለማርያም የሱዳን ጉብኝት

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 20 2005

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሜንና ደቡብ ሱዳን ከወራት በፊት የፈረሙትን የሰላም ስምምነት ተፈጻሚ እንዲደርጉ ግፊት ለማድረግ ትናንት ወደ ሱዳን መዲና ካርቱም ተጉዘዋል።

https://p.dw.com/p/179gx
Sudan's President Omar Hassan al-Bashir (L) meets his host, the new Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, at the Palace in capital Addis Ababa September 23, 2012. Leaders from Sudan and South Sudan will meet on Sunday for the first time in a year to try to agree on border security so that South Sudan can start exporting oil again, a lifeline for both economies. REUTERS/Tiksa Negeri (ETHIOPIA - Tags: POLITICS BUSINESS CIVIL UNREST)
አል በሽርና ኃያለ ማርያም ባለፈው መስከረምምስል Reuters

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት ከፕሬዚዳንት አልበሽር ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ዛሬ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር ለመወያየት ወደ ጁባ መጓዛቸዉም ተገልጿል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በሁለቱም ሱዳኖች መካከል የሰፈነውን ችግር የመፍታት አካል መሆኑ ቢገለፅም፤ የሁለቱ ሱዳኖች አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ጸጥታ ላይ ተጽዕኖ እንዳለውም ተመልክቷል።

Sudan's President Omar Hassan al-Bashir (L) meets his host, the new Ethiopian Prime Minister Hailemariam Desalegn, at the Palace in capital Addis Ababa September 23, 2012. Leaders from Sudan and South Sudan will meet on Sunday for the first time in a year to try to agree on border security so that South Sudan can start exporting oil again, a lifeline for both economies. REUTERS/Tiksa Negeri (ETHIOPIA - Tags: POLITICS BUSINESS CIVIL UNREST)
አል በሽርና የሱዳን ተደራዳሪዎች አዲስ አበባ ውስጥምስል Reuters

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት ከሰሜን ሱዳን አቻቻው ፕሬዚዳንት አልበሽር ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞ ዓላማ በሁለቱ ሱዳኖች መካከል በአዲስ አበባ የተደረሰው ስምምነት ተፈጻሚነት እንዲያገኝ ግፊት ለማድረግ መሆኑ ተገልጿል። ከዓመት በፊት የተካሄደውን የሱዳን ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ በሁለቱ ሱዳኖች መካከል የተከሰተው አለመግባባት መፍትሔ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ጥረት ስታደርግ ነበር ይላሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፥ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዞም የዚህ ጥረት አካል ነው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ጋር ከተነገጋገሩ በኋላ የሱዳኑ መሪ አልበሽር ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ሳልቫ ኪር ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን መግለጻቸውን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል። የፕሬዚዳንቱን ንግግር ተከትሎ ምናልባት ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በመስከረሙ ስምምነት መሰረት በመካከላቸው ያለውን ልዩነት አስወግደው ተቋርጦ የነበረውን የዘይት ምርት አቅርቦት ይጀምራሉ ተብሎ ይገመታል።

ሆኖም ግን በአዲስ አበባ በተደረሰው ስምምነት መሠረት ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በሁለቱ ሀገራት ድንበሮች ላይ የሰፈሩ ወታደሮቻቸውን አላስነሱም። ከጦር እንቅስቃሴ ነጻ የሆነ ቀጠናን ማቋቋም ለዘይት ምርት መጀመር አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑ ይነገራል። በቀን 350,000 በርሜል ዘይት ታመርት የነበረ ደቡብ ሱዳን፣ ከሱዳን ጋር በተፈጠረው የዘይት ማስተላለፊያ ቧምቧ ዋጋ አለመስማማት ምክንያት እየተገባደደ ባለው የፈረንጆች ዓመት ጥር ወር ምርቱን አቋርጣ ነበር። ደቡብ ሱዳንም የዘይት ምርቷን በዓመቱ መጨረሻ ለማስጀመር አቅዳ እንደ ነበር ይታወሳል።


ከሁለት ሳምንታት በፊት የአፍሪቃ ህብረትና የምዕራብ ሀገራት ተወካዮች አልበሽርና ሳልቫ ኪር በመካከላቸው የተፈጠሩ አለመግባባትን ለመፍታት በአፋጣኝ ተገናኝው እንዲመክሩ ጥሪ አቅርበውላቸዋል። በዚህም መሠረት ሁለቱም ሱዳኖች ተወካዮች በመጪው የፈረንጆች ዓመት ጥር ወር አጋማሽ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ መነጋገር እንዲጀምሩ ታቅዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአልበሽር ጋር ከተነጋገሩ በኃላ ዛሬ ወደ ጁባ ተጉዘዋል። በዚያም ከፕረዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ይነጋገራሉ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ በሱዳንና ደቡብ ሱዳን ፖሊቲካ ውስጥ ጉልህ የአደራዳሪነት ሚና ስትጫወት ይታያል። በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተካሄደ የነበረውን የፖሊቲካ ሽኩቻን ይፈታል ተብሎ በታመነው የመስከረሙ የአዲስ አበባ ድርድር፤ ኢትዮጵያ ዋና አደራዳሪ ነበረች። ምክንያቱም የሱዳንና ደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሁኔታ በኢትዮጵያ ጸጥታ ላይ ተጽዕኖ ስላለው ነው ይላሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ።

(L-R) Pagan Amum, south Sudan chief negotiator, South Sudan's President Salva Kiir, former president of Nigeria Abdulsalam Abubakar, Chief African Union mediator Thabo Mbeki, former Burundi president Pierre Buyoya and President of Sudan Omar Hassan al-Bashir meet during talks in Ethiopia's capital Addis Ababa September 24, 2012. Leaders from Sudan and South Sudan will meet on Sunday for the first time in a year to try to agree on border security so that South Sudan can start exporting oil again, a lifeline for both economies. REUTERS/Tiksa Negeri (ETHIOPIA - Tags: BUSINESS COMMODITIES POLITICS)
ሳልቫ ኪርና አልበሽር ከአደራዳሪው ኤምቤኪ ጋርምስል Reuters

ገመቹ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ