የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጤንነት ጉዳይ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 10 2004ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ በአዲስ አበባ በይፋ አለመታየታቸው፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይትም ሆነ ትናንት በተጠናቀቀው የአፍሪቃ ህብረት ጉባዔ ላይ አለመገኘታቸው ብዙ እያነጋገረ ነው። ስለዚሁ ጉዳይ በአዲስ አበባ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካልንም፤ በብራስልስ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተያየት ለማግኘት በኢሜይል ብንጠይቅም ዜናው ውሸት እና የተሳሳተ ነው በሚል ያቀረብነውን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል። በመሆኑም፡ ብራስልስ የሚገኘው ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ጠቅላይ ሚንስትር መለስ በዚያ ሕክምና እያደረጉ ነው ስለመባሉ በበኩሉ የሰማው እንዳለ ጠይቄው ቀጣዩን መልስ ሰጥቶኛል።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ