1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጎሳ ግጭት እና ጋምቤላ

እሑድ፣ የካቲት 6 2008

ጋምቤላ ዉስጥ በሁለት ግለሰቦች መካከል የተነሳ ግጭት ወደጎሳ ግጭት አድጎ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወት እንደጠፋበት ተሰምቷል። የአካባቢዉ ኗሪዎች የክልሉ መንግሥት ግጭቱን ፈጥኖ እንዳልተቆጣጠረዉ ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/1Hue9
Landverpachtung an ausländische Investoren in Äthiopien
ምስል DW

የጎሳ ግጭት እና ጋምቤላ

የመንግሥት ኃይሎች ጣልቃ ከገቡ በኋላም ቢሆን አሁንም በከተማ ዉስጥ ካልሆነ በቀር በገጠሩ አካባቢ ስጋት መኖሩን ያስረዳሉ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያዋ ግዛት በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱ ግጭቶች ወደጎሳ ግጭት እየሰፋ ብዙ ጉዳት ሲያደርስም ቆይቷል። በሀገራቸዉ የዘለቀዉ የእርስ በርስ ጦርነት ከየመኖሪያቸዉ ካፈናቀላቸዉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች አንዳንዶቹ ከነጦር መሣሪያቸዉ ድንበር ተሻግረዉ መግባታቸዉም ችግሩን እንዳባባሰዉ የሚናገሩም አሉ። ዶቼ ቬለ በዚህ ሳምንት በጋምቤላ የሚታየዉን የጎሳ ግጭት አስመልክቶ ዉይይት አካሂዷል። ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ