የጎርደን ብራውን ፈተና
ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2001ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአካባቢና የማዘጋጃ ቤቶች ምርጫ ጥቂት ድምፅ ያገኘው ሌበር ባለፈው ሳምንት መጨረሻው የአውሮፓ ፓርላማ ምርጫ ደግሞ ታይቶ የማይታወቅ ክስረት ነው የደረሰበት ። የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን በገንዘብ ሚኒስትርነታቸው ዘመን የተደነቁ ቢሆንም የዛሬ ሁለት ዓመት ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ግን የአመራር ችሎታቸው ጥያቄ ውስጥ ወድቋል ። የሌበር ፓርቲ አባላት ብራውን ከስልጣን እንዲወርዱ መጠየቅ ከጀመሩ ሳምንታት ተቆጥረዋል ። የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ድልነሳ ጌታነህ / ሂሩት መለስ /ሸዋዬ ለገሠ