የግንቦት ሰባት ተጠርጣሪዎች ችሎት ውሎ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 28 2001ማስታወቂያ
ችሎቱ ዓቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎች ላይ አለኝ ያለውን የምስክሮችና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ በመጨረሱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ቀጥሮ ይዞ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ በነዚሁ ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ሰፊና ውስብስብ በመሆኑ ገና የመጨረሻ ስራ እንደቀረው በማመልከት ለፊታችን ሀሙስ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዞ የዛሬውን ውሎውን አብቅቶዋል።
ታደሰ እንግዳው/አርያም ተክሌ/ተክሌ የኋላ