የግንቦት ሃያ ለዉጥና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አስተያየት
ሐሙስ፣ ግንቦት 20 2001ማስታወቂያ
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሸማቂ ቡድን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ደርግ መራሹን መንግሥት በሐይል አስወግዶ ሥልጣን የያዘበት አስራ-ሥምንተኛ አመት ዛሬ ተከብሮ ዉሏል።ዕለቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብሔራዊ በአል ከመሆኑ በስተቀር ግን ወትሮ እንደሚደረገዉ የአደባባይ ድግሥም ሆነ ሕዝባዊ ሥነ-ሥርዓት የለም።ዕለቱን አስመልክተን ያነጋገርናቸዉ አንዳድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ባለፉት አስራ-ሥምንት አመታት ሥለታየዉ ለዉጥ ያላቸዉ ስሜት ቅይጥ ነዉ።የጥቂቱን እነሆ።
ታደሰ እንግዳው/ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ