1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ ፕሬዚደንት የበርሊን ጉብኝት

ረቡዕ፣ ጥር 22 2005

የግብፅ ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ ለመጀመሪያ ይፋ ጉብኝት ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን በገቡበት ጊዜ የጀርመን መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሙሉ ወታደራዊ ክብር አቀባበል አደረጉላቸው።

https://p.dw.com/p/17UeK
Berlin/ Bundeskanzlerin Angela Merkel (CDU) steht am Mittwoch (30.01.13) in Berlin bei einer Pressekonferenz im Bundeskanzleramt neben dem aegyptischen Praesidenten Mohammed Mursi. Merkel und Mursi trafen sich, um ueber die innenpolitische Lage in Aegypten zu sprechen. (zu dapd-Text) Foto: Oliver Lang/dapd
ምስል dapd

ግብፃዊው ፕሬዚደንት በተለያዩ የሀገራቸው ግዛቶች ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ በቀጠለው ሁከቱ የተነሳ ለሁለት ቀናት አቅደውት የነበረውን ጉብኝታቸውን ወደ ጥቂት ሰዓታት ማሳጠር ግድ ሆኖባቸዋል። ቀውስ የገጠመው የግብጽ ፖለቲካዊ ሁኔታም የጀርመናዊትዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ ውይይት ያተኮረበት ዋነኛ ጉዳይ ነበር።

የግብፅ ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ የጉብኝት ዓላማ የሚከተሉት ፖሊሲ ዴሞክራሲያዊና ትክክለኛ መሆኑን በዚህ ሣምንት በጀርመን እና በሌሎች አውሮጳውያት ሀገራት በመዘዋወር  ማግባባትና ለሀገራቸው የፊናንስ ርዳታ እና የውጭ ካፒታል ማፈላለግ ነው።  ሆኖም፡ የቀድሞው ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ ከሥልጣን የተወገዱበት ዓብዮት ሁለተኛ ዓመት ከያዘበት ካለፈው ዓርብ ወዲህ በስዌዝ ቦይ አካባቢ በሚገኙ ሦስት ግዛቶች፡ ብሎም፡ በፖርት ሰይድ፡ ኢዝማልያ እና ስዌዝ አሳሳቢ የፖለቲካ ቀውስ እንደገና ተቀስቅሶ ቢያንስ ስድሳ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የግብፅ ጦር ኃይል ሀገሪቱ የምትፈራርስበት ሥጋት መደቀኑን ያሰማውን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ፕሬዚደንቱ ጀርመንን ብቻ ዛሬ ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ጎብኝተው ለመመለስ ወስነዋል።
ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ የቀድሞው የሀገራቸው ርዕሰ ብሔር ሆስኒ ሙባረክ ከሥልጣን ከተወገዱ ከሁለት ዓመት በኋላ አሁን እንደገና የሚታየውን የሕዝቡን ቁጣ እንዴት ሊያበርዱት ይችላሉ በሚለው ጉዳይ ላይ ሁለቱ መሪዎች ተወያይተዋል።
ጀርመን በጠቅላላ የግብፅ የፖለቲካ ኃይላት መካከል ውይይት እንዲካሄድ እንደምትፈልግ እና የካይሮ መንግሥትም የሰብዓዊ መብቶችን እንዲኢከብር ከፕሬዚደንት ሙርሲ ጋ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለ?ጫ ወቅት አሳስበዋል።
ግብፃዊው ፕሬዚደንት በሀገራቸው ዴሞክራሲያዊውን መመሪያ እንዲከተሉ እና የሀገሪቱ ተቀናቃኝ ወገኖች በጠቅላላ ለፖለቲካው ውዝግብ በውይይት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ አሳስበዋል። ጀርመን ግብጻዊውን ፕሬዚደንት ተቀብላ ማስተናገድዋ ስህተት ነው በሚል አንዳንዶች ነቀፌታ ሰንዝረዋል። ይሁንና፡ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ ማንኛውም ዓብዮት ካላንዳች እክል እንደማይካሄድ እና ለሚያጋጥሙት ሽንፈቶችም በሂደት መልስ ማግኘት እንዳለበት የሚታወቅ እንደመሆኑ መጠን ለፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ ፡ ዴሞክራሲያዊውን መርህ እስካከበሩ ድረስጊዜ፡ ለግብፅ ዓብዮትም ዕድል ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።
« ምንም እንኳን በግብፅ የሚታየውን ሂደት የምንነቅፍበት ሁኔታ ቢኖርም፡ ከዚችው ሀገር ጋ የጀመርነውን ውይይት መቀነሱ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ መድረስ ይሆናል። በአንፃሩ፡ ውይይታችንን ማጠናከር ነው የሚገባን። ይህንን በምናደርግበት ጊዜ ብቻ ነው በግብፅ ላይ ተፅዕኖ ልናሳርፍ የምንችለው፤ ለምሳሌ ሲቭሉን ማህበረሰብ በማጠናከሩ ተግባር ላይ። »
ቬስተርቬለ እእክለው እንዳስረዱት፡ በአሁኑ ጊዜ በግብፅ የሕዝቡ ቁጣ ይቀዘቅዝ ዘንድ በዚችው ሰሜን አፍሪቃዊት ሀገር ዴሞክራሲያዊው ሥርዓት የሚጠናከርበትን መንገድ ማገዝ ይሆናል።
« በወቅቱ በግብፅ በሚታየው ሥዕል ንዴት የሚሰማውን እና ይህንኑ ብርቱ ቁጣውንም በተቃውሞ የሚያሳየውን ማንኛውንም ግለሰብ በሚገባ እረዳለሁ። ግን የኛ ተግባር መሆን ያለበት ግብፅን በጀመረችው ዴሞክራሲያዊ ሂደት ላይ ማበረታታት ይሆናል። »   የግብፅ ፕሬዚዳንት ሙርሲ ያቀረቡትን ብሔራዊ የውይይት ሀሳብ እንደማይቀበለው አስታውቆ የነበረው የተቃዋሚው ወገን መሪ መሀመድ ኤል ባራዳይ ዋነኞቹ የሀገሪቱ የፖለቲካ ኃይላት ከፕሬዚደንቱ ጋ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያካሂዱ ዛሬ ጥሪ አስተላልፈዋል። የዚሁ ስብሰባ ዓላማም በወቅቱ የስድሳ ሰዎች ሕይወት ያጠፋው ግጭት የሚያበቃበትን መፍትሔ ማፈላለግ እና የምሩን ውይይት መጀመር እንደሚሆን ኤል ባራዳይ አስረድተዋል።
ወደ ሰባ የሚጠጉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በመራሒተ መንግሥት ሜርክል ጽሕፈት ቤት ደጃፍ በመሰብሰብ በፕሬዚደንት ሙርሲ ጉብኝት አንፃር ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸውን የበርሊን ከተማ ፖሊስ ገልጾዋል።

A woman holding an Egyptian flag shouts slogans during a protest in front of the chancellery against the visit of Egyptian President Mohammed Morsi prior to a meeting of him with German Chancellor Angela Merkel in Berlin, Germany, Wednesday, Jan. 30, 2013. (Foto:Markus Schreiber/AP/dapd)
ምስል dapd
Ausgebrannter Mannschaftstansporter der Polizei auf dem Tahrirplatz in Kairo, 29.1.13; Copyright: Matthias Sailer
ተቃውሞ በግብፅምስል Matthias Sailer

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ